የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ የጋራ ዕሴቶቻችንን...

image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ የጋራ ዕሴቶቻችንን ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።

የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ የጋራ ዕሴቶቻችንን ማስቀጠል እንደሚገባ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማችን ነዋሪዎች የጋራ ዕሴቶቻቸውን በመቻቻል አስቀጥለው  እንዲሄዱ"ለሀገርና ለትውልድ ግንባታ" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለትም የቢሮው የኃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ ከአስራንዱም ክ/ከተሞች የተወጣጡ  ወጣቶች ጋር  ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ በመገኝት መድረኩን የመሩት አቶ ሙልቀን እንየው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የኃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ፣ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ የሰላም ተሞክሮዎች በማነጻጸር፣ማህበራዊ ትስስርና የሽምግልና ዕሴት እንዲዳብር፣የተሞክሮ ስም ዕድርና የጋራ ስራና ማህበራዊ እርቅ እንደሁም ኪነ 
-ጥበብ ለሰላምን በመጠቀም እና ዋና ትኩረት በማድረግ አለመግባባቶችን በፍርድ ቤት  ፈንታ በአከባቢው በዕርቅና በሰላማዊ ውይይት በመፍታት፣ከዕርስ በዕርስ ጦርነት ይልቅ ማህበረሰቡን በጋራ ልማትና በይቅርታ በማቀራረብ፣ውጤት ማምጣት እንደሚቻልም ገልጸዋል።

የከተማውን ሰላምና ደህንነት አጠናክሮ ለማስቀጠል ልዩነትን ዕውቅና በመስጠት፣ለአስተያየት ክፍት መሆንን በመረዳት፣የአከባቢያቸውን ሰላም በማስጠበቅ እና በከተማው ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከልና በመቆጣጠር ወጣቶች ኃላፊነታቸውን  መወጣት ይገባል ብለዋል። 

ዳይሬክተሩ አክለውም የከተማውን ብሎም የሀገርን ሰላም ለማስጠበቅ ከወጣቶች የሚጠበቁ ግለሰባዊና ማህበራዊ ኃላፊነቶችን ከግምት በማስገባት ስሜትን መቆጣጠር እንዳለባቸውም አሳስበዋል።

ሰኔ 18/2018 ዓ.ም

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!

ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79