በተያዘው በጀት አመት ቢሮው የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በተገቢው መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ችሏል ።
በተያዘው በጀት አመት ቢሮው የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በተገቢው መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ ችሏል ።
አቶ ጌታሁን አበራ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ
ሰኔ 18/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ቢሮው በዋናነት የሚሰራውን ስራ ለህብረተሰቡ በተቀላጠፈና ፈጣን የሆነ መረጃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እያደረገ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ከጸጥታ ስራ አኳያና በፍክት ቼኪንግ ዙሪያ ለቢሮው ዳይሬክሮች፣አስተባባሪዎች፣ቡድን፣መሪዎች ኮሙኒኬሽን ተወካዩች፣ባለድርሻ አካላት በተገኙበት የግንዛቤ መፍጠርና የተሰሩ ስራዎች ዙረያ ውይይት በማድረግ የቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል።
በውይይቱ ላይ አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው በተያዘው በጀት አመት እጅግ በርካታ ስራዎችን በመስራትና የተሰሩ ስራዎችን በተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦች ለህብረተሰቡ መረጃን ተደራሽ ማድረግ ችለናል ብለው ከከተማውን ነዋሪዎችና የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ነዋሪውን በማሳተፍ ወንጀልን በመከላከልና ስጋትንም በመቀነስ ህግ የማስከበር ስራዎችንም መሰራታቸውንም አስታውሰው በቅርቡ የተካሄደው ሀገር አቀፍ ምርጫን ጨምሮ ከጅማሮው እስከ ውጤቱ እስኪገለጽበት ድረስ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ተደራሽ እንዲሆን የማድረግም ስራ መሰራቱን አብራርተዋል።
በቀጣይም እንደ ከተማ አስተዳደር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተደራሽ የማድረግ ስራን አጠናክሮ ማስኬድ እንደሚገባ ገልፀው የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ስራው አቅም ጠንካራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ እውነተኛና ሀሰተኛ መረጃን በመለየት እውነተኛ ሚዲያን በመከተል ሀሰተኛ ሚዲያዎችን በመታገል በኩል ስራዎችን በጋራ መስራት እንደሚገባና የሚሰሩ ስራዎችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ህብረተሰቡ ከሀሰተኛ መረጃዎች እራሱን መጠበቅ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ወ/ሮ ዓለም አበበ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ቢሮው ከተሰጠው ተልዕኮና ከያዘው ዕቅድ አኳያ በህዝብ ግንኙነትና በማህበራዊ ሚዲያ በተለያዩ አማራጮች ተደራሸ የማድረግ ስራ የተከናወኑ መሆኑን ባቀረቡት አፈፃፀም ላይ ያመላከቱ ሲሆን አያይዘውም እንደ ቢሮ የህዘብ ግንኙነቱን ስራ ተሳትፊውን አብሮ በማጠናከር አዲስ አበባ ላይ ያለውን የሰላም የደህንነት ስራ በጽንፍ ሀይሎች ሴራ በማክሸፍና የሚዲያ ንቁ ተሳታፊ በመሆን እውነተኛ መረጃ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመው ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ በማዋል የፀጥታና መሰል ጉዳዮችን የማሳወቅ ስራ በመስራት የከተማን ሰላም ማረጋገጥ ላይ የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል ።
አቶ ናኦድ ጌታቸው በፍክት ቼኪንግና ስለ እውነተኛና ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዴት መለየት እንደሚገባ ስልጠና ሰጥተዋል።
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!
ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79