የአዲስ አበባ ከተማ የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንኡስ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው የግምገማ መድረክ የቀጣይ ሶስት ወራት ትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።
የአዲስ አበባ ከተማ የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንኡስ ኮሚቴ ዛሬ ባካሄደው የግምገማ መድረክ የቀጣይ ሶስት ወራት ትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።
እነዚህም፣
1. የህግ የበላይነት የማስከበር ስራ የበለጠ በማጠናከር ያለንግድ ፈቃድ፣ ንግድ ፈቃድ ሳያድሱ፣ የአድራሻ ለውጥና መሰል ህገ ወጥነት ላይ የተሰማሩ ነጋዴዎችን የመከታተል፣ የመቆጣጠር ፣ ህጋዊ እርምጃ መውሰድና ወደ ህጋዊ ስርአት እንዲገቡ ማስቻል፣
2. የቅዳሜና ዕሁድ የገበያ ማዕከላት ላይ የምርት አቅርቦትና በተለጠፈው ዋጋ ግብይት እየተካሄደ መሆኑን ቀረብ ብሎ መደገፍ፣ ክትትል ማድረግና የህብረተሰቡን የኑሮ ሁኔታ ጫና እንዲያቀሉ ቁጥጥር ማድረግ፣
3. የመጋዘን አሰሳና ፍተሻ በማድረግ ምርት አከማችተው የሚያስቀምጡ ነጋዴዎችን የቁጥጥር ስራ በመስራት የምርት እጥረት እንዳይኖር ማድረግ ፣
4. በከተማዋ አምስቱም የመግቢያና መውጫ በሮች ጥብቅ አሰሳና ፍተሻ ማድረግና ከሸገር ከተማ ጋር በቅንጅት መስራት፣
5. የኮንትሮባንድ ቁጥጥር ላይ የተጀመሩ ስራዎችን ማጠናከር፣
6. የሸማች ህብረት ስራ ማህበራት የድጎማ ምርቶችንና ሌሎች ግብአቶች ለታለመለት አላማ እየዋለ ስለመሆኑ መከታተል፣
7. የገበያ ማዕከላት ላይ ያለው የምርት አቅርቦትና የዋጋ ሁኔታን መከታተልና ከደላላ ነፃ የሆነ ግብይት ስለመፈፀሙ ማረጋገጥ ፣
8. በዋና ዋና መንገዶችና የምሽት ንግድ ስርአት ተግባራዊነት በአግባቡ ፈትሾ ስራውን ማጠናከር፣
9. የነዳጅ የአቅርቦትና ስርጭት ማደያዎችን ማእከል በማድረግ ጥብቅ ክትትል ማድረግ፣
10. ያለደረሰኝ አየር ባየር የሚሰሩ ነጋዴዎችን የመቆጣጠርና ህጋዊ እርምጃ መውሰድና የማታና የቀን የመኪና ቁጥጥር ማድረግ፣
11. ከገቢ ስራዎቻችን አንፃር በከተማችን የገቢ አሰባሰብ ስርአቱ ህጋዊነት ባለው መልኩ መሰብሰብ ፣
12. የግብይት ስርአቱ በደረሰኝ ብቻ እንዲፈፀም ማድረግና ወደ ቫት ስርአት ያልገቡትን ተከታትሎ ማስገባት የቀጣይ የርብርብ ማእከላት በማድረግ በትኩረት እንዲሰራ የንዑስ ኮሚቴው ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ አሳስቧል።