በከተማችን ህጋዊ ስርአት ያለው የንግድ ስርአት በመዘርጋት ለነዋሪው ቀልጣፋና ጥራት ያለው የግብይት ሂደት እንዲኖርና ህጋዊነትን የማስፈን ስራዎች መስራት ተችሏል።
በከተማችን ህጋዊ ስርአት ያለው የንግድ ስርአት በመዘርጋት ለነዋሪው ቀልጣፋና ጥራት ያለው የግብይት ሂደት እንዲኖርና ህጋዊነትን የማስፈን ስራዎች መስራት ተችሏል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የንዑስ ኮሚቴው ሰብሳቢ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴ የ7ወራት የተከወናወኑ ተግባራትን በመገምገም የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጧል።
ንዑስ ኮሚቴው በበጀት ዓመቱ በከተማው ህጋዊ ስርአትን ከማስጠበቅ አንፃር የተከናወኑ የቅዳሜና ዕሁድ የገበያ ቦታዎችን የማስፋትና የአቅርቦት ጥራት በተመለከተ ፣ ህገወጥ ነጋዴዎች ወደ ህጋዊ ስርአት የማስገባት ፣ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈፅሙ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር በማድረግ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ ፣ በነዳጅ ግብይት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ወንጀለኞችን ተጠያቂ ማድረግ ስራን በትኩረት ሲሰራ መቆየቱ ተመላክቷል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የግብረሀይሉ ሰብሳቢ እንዳሉት ንዑስ ኮሚቴው በከተማው ውስጥ ህጋዊ የግብይት ስርአት ጥሰቶችን መቆጣጠርና ህጋዊ እርምጃ በመውሰድ በከተማው ህጋዊ መሰረት እንዲኖር ማድረግና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ዋና ተልዕኮው እንደመሆኑ ባለፉት ሰባት ወራት በርካታ ውጤታማ ስራዎች መሰራቱን አብራርተዋል።
ንዑስ ኮሚቴው ህጋዊነትን ባልተከተሉ አካላት ላይ ህጋዊ እርምጃ ከመውሰድ በተጨማሪ ግንዛቤ በመፍጠርና በማስተማር ወደ ህጋዊ ስርአት እንዲገቡና ስራቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ እንደሚገባ የገለፁት የቢሮ ኃላፊዋ በቅንጅት የሚሰሩ ስራ
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ እንዳሉት ህገወጦች ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ፣ ከነዳጅ ጋር በተፈጠረው የአቅርቦት እጥረት በቅንጅት መስራት በመቻላችን ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አብራርተዋል። አክለውም ከቅዳሜና ዕሁድ የግብይት ሂደትና ጥራት ያለው ምርት እንዲቀርብ ከማድረግ አንፃር የተሰሩ ስራዎች አመርቂ መሆናቸውን አንስተው ይህን የቅንጅት ስራ በቀጣይ ወራትም አጠናክሮ በማስቀጠል በተለይም ያለንግድ ፈቃድ የሚሰሩ ነጋዴዎችና ህግን በሚጥሱ አካላት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የህግ ስርአትን ማስፈን ከንዑስ ኮሚቴው እንደሚጠበቅ አስቀምጠዋል።
አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ የንዑስ ኮሚቴውን የሰባት ወራት አፈፃፀምን ሲያቀርቡ እንዳሉት የቅዳሜና ዕሁድ የገበያ ቦታዎችን የማስፋትና የአቅርቦት ጥራት በተመለከተ ፣ ህገወጥ ነጋዴዎች ወደ ህጋዊ ስርአት የማስገባት ፣ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈፅሙ ነጋዴዎች ላይ ቁጥጥር በማድረግ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ ፣ በነዳጅ ግብይት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ወንጀለኞችን ተጠያቂ ማድረግ መያሉን በዝርዝር አቅረበዋል።
በከተማው አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ስግብግብ ነጋዴዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ፣ ህጋዊ ስርአትን የማይከተሉ ነጋዴዎችን ወደህጋዊ ስርአት እንዲገቡ ማድረግ እና መሰል ተግባራት ላይ በርካታ ስራዎች መስራት መቻሉን የንዑስ ኮሚቴው አባላት የገለፁ ሲሆን በቀጣይም በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በቅንጅት መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ንዑስ ኮሚቴው የሰባት ወራት አፈፃፀም ግምገማውን ሲያጠቃልል የነበሩ ጥንካሬዎችን በማስቀጠል እንዲሰራና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በዝርዝር አስቀምጧል።
የህግ ማስከበርና ቁጥጥር ንዑስ ኮሚቴው ከመአከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የሰላምና ፀጥታ የስራ ኃላፊዎች ፣ የንግድ ፣ የደንብ ማስከበር ፣ የፖሊስ አካላትና የገቢ የስራ ኃላፊዎችን አቅፎ የያዘ መሆኑ ይታወቃል።
ሰኔ 16/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!
ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79