የህዝብ ቅጥር ጥበቃዎች የከተማው ሰላም ለማስጠበ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የህዝብ ቅጥር ጥበቃዎች የከተማው ሰላም ለማስጠበቅ ከምንጊዜውም በበለጠ መልኩ ተጠናክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል።

የህዝብ ቅጥር ጥበቃዎች የከተማው ሰላም ለማስጠበቅ ከምንጊዜውም በበለጠ መልኩ ተጠናክረው መስራት ይጠበቅባቸዋል።

አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ 

              16/10/2018 ዓ.ም
               **አዲስ አበባ*

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር  ቢሮ የከተማውን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ሌት ተቀን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የቢሮው የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ለአዲስ የህዝብ ቅጥር ጥበቃዎች "በወንጀል መከላከል በስነ ምግባርና በህዝብ ቅጥር ጥበቃ ላይ ያላቸው ሚና " በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ በመገኝት መድረኩን የመሩት አቶ ፍስሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሲሆኑ  ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ብሎም ውጤቱ እስኪገለጽበት ድረስ ባለው ሂደት ላይ የጠላትን ሀይሎች ሴራ በጋራ በመሆን ማክሸፍ በመቻላችን ውጤቱንም ማየት ችለናል ያሉት ሀላፊው ለነበረው የተጋ ብርታትና ጥንካሬያችሁ ምስጋና ይገባችኋል በማለት አሁንም ወደፊትም የከተማውን ሰላምና የደህንነት አጠናክሮ ማስቀጠል  ይገባልም ብለዋል።  አክለውም የከተማውን ሰላም ማስጠበቅ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን በመረዳት ሀላፊነታቸውን ጥበቃዎቹ የበለጠ እንዲወጡና በጋራም በመሆን ትኩረታችንን አሁንም ከተማው ላይ በማድረግ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ከስሩ  መከላከልና መቆጣጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።

ሀላፊው አያይዘውም የሀገርን ሰላም የማይፈልጉ የጠላት ሀይሎች አሁንም ስላሉ እርስ በርስ የሚከፋፉሉ  የኢትዩጽያን ሀያልነትና ለውጥ ማየት የማይፈልጉ ግለሰቦች ስላሉ አሁንም ወደፊነትም ተጠናክሮ እርስ በርስ ስለሰላም በመወያየት ለጠላት ሀይሎች ዕድል ባለመስጠት የከተማውን ሰላም በጋራ በማስጠበቅ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ከአደራ ጭምር ተናግረዋል ።

ኮማንደር ሙሉጌታ በጋሻው የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳንሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው  የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ ሀላፊነታቸውን መወጣታቸው የሚያስደስት መሆኑን  ጠቁመው  የወንጀል አስከፊነትን  ፣ የሰላምን ሀያልነት በመረዳት መሰረታዊ የሆነውን ሰላምና በቀጣይም አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባልም ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ አብርሃም እንግዳ ወርቅ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ለውይይቱ የሚሆነውን መነሻ ጹሁፍ ያቀረቡ ሲሆን ስለ ወንጀል ምንነት፣መርሆዎቹ፣አይነቶች፣ስለሚያስከትለው ጉዳት፣ስለ ቅድመ ዝግጅት፣የአዕምሮ ዝግጁነት፣የወንጀል አይነቶች፣ዘዴዎቹ ስልቱ ፣ስለ መብትና ግዴታዎች አጠቃላይ ስለ ውይይቱ አስፈላጊነት አብራርተዋል።

የውይይቱ ዓላማም የአካባቢን ብሎም የሀገርን ሰላም ለማስፈን በመደራጀት ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የከተማውን ሰላም በጋራ ማስጠበቅ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል ከህዝብ ቅጥር ጥበቃዎቹ ለተነሳው ሀሳብና አስተያየት የዘርፉ ሀላፊ ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዋል።

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!

ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79