የህዝብ አደረጃጀት መረጃዎችን በቴክኖሎጂ መለዋወጥ የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ በማበልፀግ ወደ ስራ መገባቱ ተገለፀ።
የህዝብ አደረጃጀት መረጃዎችን በቴክኖሎጂ መለዋወጥ የሚያስችል አዲስ ቴክኖሎጂ በማበልፀግ ወደ ስራ መገባቱ ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ በመስጠት የተገልጋይን እርካታ ከፍ በማድረግ ላይ ይገኛል።
ከዚህም ውስጥ በህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት መረጃዎችን የመለዋወጫ ሲስተም ፣ የሰራዊቱን ሙሉ መረጃ የሚያጠናቅር ፣ በየወረዳ የሚሰሩ ስራዎችን ሪፖርት የሚያዘጋጅ እንዲሁም ከወረቀት ነፃ የሆነ የመረጃ ቅብብሎሽ ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ባለማው መሰረት ለዘርፉ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ አመራሮችና የአይሲቲ ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል።
አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በዘርፉ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የሰላም ሰራዊት በመፍጠር በሰባት ዙር ከ200 ሺ በላይ ህዝባዊ አደረጃጀት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉን አስታውሰው ዛሬ ግንዛቤ የተፈጠረው ቴክኖሎጂ የዚህን ህዝባዊ አደረጃጀት መረጃን በቴክኖሎጂ መያዝ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።
ኃላፊው አክለውም ከተማዋ ሰላሟ የተረጋገጠባት ህዝቦቿ በሰላም ወጥተው መግባት እንዲችሉ ለማስቻል የተደራጁ የህዝብ አደረጃጀቶችን መረጃን በተደራጀና በቴክኖሎጂ መያዝና ማጥራት አስፈላጊ መሆኑንና ይህም የተናበበ የፀጥታ ስምሪት ለመስጠትና ወንጀልንና ወንጀለኞችን ለመቀነስ አጋዥ መሆኑን ገልፀው ሁሉም የፀጥታ መዋቅር ቴክኖሎጂውን በመጠቀም የጠራ የሰላም ሰራዊት እንዲኖርና የከተማዋን ሰላም በባለቤትነት የመምራት ስራን በትኩረት እንዲሰራ አሳስበዋል።
በቢሮው የለሙ ቴክኖሎጂዎች ወደ ስራ ከገቡ ጀምሮ በርካታ ውጤታማ ስራዎች መስራት መቻሉን የገለፁት የቢሮው አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው አመራሩ ቴክኖሎጂዎቹን በመጠቀም ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግና የበለጠ ማዘመን እንደሚገባ ገልፀዋል።
በመጨረሻም ቢሮው የሚጠቀምባቸውን የለሙ ቴክኖሎጂዎችን ለተሳታፊው ገለፃ ተደርጓል።
ሰኔ 9/2018 ዓ.ም
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!
ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79