ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የወንጀል...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የወንጀል መከላከል ስራን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጠ።

ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የወንጀል መከላከል ስራን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አቅጣጫ ተሰጠ።

በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የፀጥታና የወንጀል ምጣኔን ቅነሳ ፣ የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታን ማፅናትና የከተማዋን ሰላም በዘላቂነት ማስፈንና የልማት ግስጋሴዋን ማስቀጠል ብሎም በርካታ የአደባባይ ኩነቶች ያለምንም የፀጥታ ችግር ማሳካት መቻሉ ህብረተሰቡ ግንባር ቀደም ተዋናይ በመሆን በባለቤትነት የሰራበት ውጤት መሆኑ የቢሮው ከፍተኛ ኃላፊዎች እሰከ ታችኛው መዋቅር አጠቃላይ ሰራተኞች ጋር ባደረጉት የውይይት መድረክ ተገልጿል።

የአዲሰ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በከተማዋ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን ፣ የሰላም እሴቶችን መገንባት ፣ የኦፕሬሽን ስራዎችን በመስራት የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉ ፣ የፀጥታ መረጃዎችን ማደራጀትና አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት እንዲሁም አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ የተሰጠበት አግባብ ላይ ውጤታማ ስራዎች መሰራቱ በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ህዝቡ የሰላምን ዋጋ በመረዳት በፀጥታ ስራ ላይ ግንባር ቀደም በመሆን የአካባቢን ሰላም በማስጠበቅና ወንጀልንና ወንጀለኞችን በመከላከል ረገድ ከፀጥታ አካሉ ጋር የሰራበት አግባብ አመርቂ እንደሆነ አንስተዋል። ኃላፊው አክለውም ያለውን የፀጥታና የወንጀል መከላከል ስራን በድህረ ምርጫና በቀሪ ወራት በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ አቅጣጫ ሰጥተዋል

ዶ/ር ወንድማገኝ ታፈሰ የቢሮው ምክትልና የፀጥታ መረጃ ዘርፍ ኃላፊ እንዳሉት በከተማችን አዲስ አበባ 7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር ማከናወን የተቻለው በመዋቅሩ ያለው ጠንካራ የመረጃ ፍሰትና ልውውጥ በመኖሩ የፀጥታ ስራን በመናበብ መሰራት በመቻሉ መሆኑን አንስተው በበጀት አመቱ የተከናወኑ የአደባባይ ኩነቶችና ሀይማኖታዊና ባህላዊ በአላቶች ያለፀጥታ ችግር ተከብረው ማለፋቸው የቅንጅት ስራ ውጤት በመሆኑና ይህን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ሀገር በቀል የሰላም እሴት ግንባታን ማስረፅና የአብሮነት ባህልን ማጠናከር ፣ የባህላዊ የእርቅ ስነስርአትን ማስቀጠል፣ከሀይማኖት ተቋማት ጋር በቅርበት መስራት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ምክትልና የሀይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ ገልፀዋል።

በውይይቱ ላይ በቢሮው በፀጥታና ኦፕሬሽን ፣ በፀጥታ መረጃና በሀይማኖትና ሰላም እሴት ዘርፍ የተሰሩ ስራዎች መነሻ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።

ሰኔ 03/2018 ዓ/ም

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!

ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79