ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በከተማው በርካታ ኩነቶች ያለፀጥታ ችግር መከናወናቸውንና የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉ ተገለፀ።
ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በከተማው በርካታ ኩነቶች ያለፀጥታ ችግር መከናወናቸውንና የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉ ተገለፀ።
ሰኔ 02/2018 ዓ/ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ
የበጀት ዓመቱ የትኩረት ግቦች ፣ ዓላማዎች እና የዕቅድ ተግባራትን በተመለከተ ውይይት ከማዕከል እስከ ወረዳ ካሉ ዳይሬክተሮች ፣ አስተባባሪዎች እና ቡድን መሪዎች ጋር ውይይት ያካሄደ ሲሆን በውይይት መድረኩም ህዝቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ በመቻሉ በከተማው በርካታ ኩነቶች ያለፀጥታ ችግር መከናወናቸውና የወንጀል ምጣኔን መቀነሱ ተመላክቷል።
አቶ ፍሰሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ እና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ እንደተናገሩት በከተማችን አዲስ አበባ የተከናወኑ በርካታ የአደባባይ በአላትና 7ኛው ሀገራዊ የምርጫ ሂደት ፍፁም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ ማለፍ የቻለው ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉት ሰራተኞች በየአከባቢያቸው በማስተባበርና ድጋፍ በማድረግ ፣ የፀጥታ አካሉ ቅንጅታዊ ስራ ከህብረተሰቡ ጋር መስራት በመቻሉ መሆኑን አንስተው በቀጣይ በድህረ ምርጫው ወቅት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።
ሀላፊው አክለውም የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በዋናነት ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ፣ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ የዜጎችን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅና ከተማዋ አስተማማኝ የሆነ ሰላሟ የተጠበቀ ከተማ እንድትሆን ማድረግ ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራቱን አንስተው በዚህም ውጤት ማምጣት መቻሉንና በቀጣይ በድህረ ምርጫና የበጀት ዓመቱ ቀሪ ስራዎች ላይ አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል።
በዋናነት የመድረኩ ዓላማ በበጀት ዓመቱ በዕቅድ ከተቀመጠው አንፃር የክንውን ሂደቱን በመገምገምና ክፍተቶች ላይ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ቀሪ ስራዎች ላይ ርብርብ በማድረግ የትኩረት አቅጣጫ አድርጎ መውሰድ እንደሚገባና የማህበረሰቡን ተሳትፎና የሰላም ባለቤትነቱን አጠናክሮ እንዲያስቀጥል እንደሆነ የዘርፉ የሰላም ሰራዊት የፀጥታ አደረጃጀትና ማህበራት ግንባታ ስምሪት ቡድን መሪ አቶ ውድነህ አቢ ለመነሻ የሚሆን ሰነድ ባቀረበበት ወቅት ገልጿል።
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!
ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79