አብሮነትና አንድነትን አጠናክሮ በማስቀጠል ለሰ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

አብሮነትና አንድነትን አጠናክሮ በማስቀጠል ለሰላም እሴት ግንባታ የበኩላችንን መወጣት ይገባል።

አብሮነትና አንድነትን  አጠናክሮ በማስቀጠል ለሰላም እሴት ግንባታ የበኩላችንን መወጣት ይገባል።

       አቶ ብርሀኑ ረታ 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ 

          ሰኔ 2/2018 ዓ.ም (PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ "መከባበርና አብሮነት ባህል ለሰላም ግንባታ" በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ከዘርፉ ባለሙያዎች፣አስተባባሪዎች ቡድን መሪዎች፣ከብሎክ የጸጥታ ኮሚቴዎች፣ከጸጥታ አካላት  ጋር ውይይት አካሂዷል። 

በውይይቱ ላይ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው የከተማው ማህበረሰብ የሰላም ባለቤትና የሰላም ዘብ በማድረግ በርካታ ስራዎችንም አብሮ በመስራት ውጤታማ የሆኑ ተግባራትን በማከናወን ግንባር ቀደም በመሆንና ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን አስታውሰው የከተማውን ሰላም በማጽናት ሰባተኛውን አገር አቀፍ  ምርጫን ጨምሮ በርካታ ከተማው ላይ የተካሄዱ ሀገር አቀፍና አለም አቀፍ ሁነቶች በሰላም መጠናቀቅ መቻሉን ገልፀዋል።

ኢትዮጲያውያን አብሮነትና አንድነት ያለን እርስ በርሳችን ተከባብረንና ተዋደን የምንኖር ህዝቦች መሆናችንን ለአለምም ህዝብ አሳይተናል ያሉት ሀላፊው ብዝሀነታችን ጌጣችን መከባበር መደማመጥ በጋራ አብሮ መቆም ከትውልድ ወደ ትውልድ የምናሻግር በአንድነት አብሮነትን በማበርከት ኢትዩጵያን በጋራ ማቅምም ችለናል ሲሉ የተደመጡ ሲሆን ኢትዩጵያዊነት ለብቻ መኖር ሳይሆን አንዱ ላንዱ መኖር ለዘመናት በመካከላችን ያለውን አንድነት ለመነጣጠል የሚተጉ ሀይሎች ቢኖሩም ለዘመናት ዋጋ በመክፈል የጸና በትውልድ ቅብብሎሽ ያለመ ዘመኑም የሚጠይቀውን በአርበኝነት ማወቅ ይገባልም ሲሉ ተደምጠዋል ።

አቶ ብርሀኑ አያይዘውም የኢትዮጵያዊያን ጉዞ በከፍታ ወቅት ላይ ያለ በእያንዳንዱ  ጉዳይ ላይ በማጤን   ታላቅነቷን  በማስቀጠል ሀገራችንን ለማሻገር በተለያየ ማህበረሰብ አቀፍ የከተማው አደረጃጀት ላይ በመሳተፍ ጠላት እንዳሰበው ሳይሆን ሀገር ሁሌም በከፍታ ደረጃ ላይ መሆኗን በማሳየት ኢትዮጵያዊነት  ሁሌ አሸናፊነት መሆኑን በማስገንዘብ በህዝብ ተሳትፎ የጸናች እንደመሆኗ ሀገር ግንባታ ላይ መንግሥት ብቻውን ሊሰራ ስለማይችል የመንግሥትን ፖሊሲና ስትራቴጂዎች ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

ባልተገባ ነገር ባለመጋጨት እርስ በርስ ከሚከፋፍሉ  የጠላት ሀይሎች በመራቅ ፈተናዎችን አብሮ በመውጣትና ወደ ጥሩ ዕድል በመቀየር አብሮነትን ባህልን በጋራ በማስቀጠል ሀገር እንደ ሀገር እንድትቀጥል ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ የጸጉረ ልውጥ እንቅስቃሴዎችን ሴራ በማክሸፍ ጥቅሙ ለጋራ ለሆነው ለሀገርና ለከተማ ሰላም አብሮ በመትጋት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማበርከት ይገባል ሲሉ አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ ተናግረዋል።

መከባበርና አብሮነት ባህል ለሰላም ግንባታ በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ የመወያያ ጹሁፍ ያቀረቡት አቶ ሙሉቀን እንየው የቢሮው የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ በቀረበው ፅሁፍ ላይም ሰፊ ውይይትም ተደርጓል።

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!

ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79