7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የፀጥታ ስራ አፈፃፀምና የድህረ ምርጫ ስራዎችን ዕቅድ በተመለከተ ግምገማዊ ውይይት ተካሄደ።
7ኛው ሀገራዊ ጠቅላላ ምርጫ የፀጥታ ስራ አፈፃፀምና የድህረ ምርጫ ስራዎችን ዕቅድ በተመለከተ ግምገማዊ ውይይት ተካሄደ።
ሰኔ 01/2018 ዓ.ም (PSAB)
የአዲሰ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከፀጥታ ጥምር ሀይል ጋር በጋራ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በከተማው የተመራበትን የፀጥታ ሁኔታና የድህረ ምርጫ የዕቅድ ስራዎችን ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ የሚገኙ ጥምር የፀጥታ አካሉ ጋር ግምገማዊ ውይይት አካሂዷል።
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በአዲስ አበባ ከተማ ፍፁም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ ጥምር የፀጥታ አካሉ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት በቅንጅት በመሆን በምርጫ ሂደቱ የፀረ ሽብር ሀይሎችና በውስጥ ባዳና በውጭ ባንዳ የታቀዱ የሽብር ጥቃቶችን ማክሸፍ መቻሉን በስፋት ተገምግሟል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ የምርጫው ሂደት ፍፁም ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ ማለፍ የቻለው የፀጥታ አካሉ ቅንጅታዊ ስራ ከህብረተሰቡ ጋር መስራት በመቻሉ መሆኑን አንስተው በቀጣይ በድህረ ምርጫው ወቅት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም የምርጫ ውጤት በምርጫ ቦርድ ይፋ እሰከሚደረግ ድረስ ከእስከ አሁኑ በበለጠና በልዩ ትኩረት የፀጥታና የደህንነት ስራን በተጠንቀቅ መጠበቅና ከህብረተሰቡ ጋር በቅርበት መስራት እንደሚገባና የወንጀል ምጣኔን መቀነስና የመከላከል ስራን ማጠናከር እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ በምርጫ ሂደቱ ላይ የፀጥታ ጥምር ሀይሉ በኮማንድ ፖስት መምራት በመቻሉ ብሎም ህዝቡ የሰላም ባለቤት ማድረግ በመቻሉ ያለምንም የፀጥታ ችግር ማጠናቀቅ መቻሉ ትልቅ ድል መሆኑን አስቀምጠዋል። ስራ አስኪያጁ አክለውም ከምርጫው በኋላ መዘናጋቶች እንዳይኖሩ በቀጣይ በትኩረትና በጥንቃቄ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።
በምርጫው ሂደት የነበሩ የፀጥታና የወንጀል መከላከል ሂደቶችን በሪፓርት ያቀረቡት የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር በከተማው ሂደቱን ለማደናቀፍ የሞከሩ በርካታ የፀረ ሰላም ሀይሎችን ሴራ በፀጥታ ጥምር ሀይሉና ከህዝቡ ጋር በቅድመ ምርጫ ሂደት የተካሄዱ የውይይትና የጋራ ስራ በመስራት ማክሸፍ መቻሉንና ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ መከናወን መቻሉን አብራርተዋል።
ኃላፊው አክለውም በምርጫ ሂደት የታየውን የመናበብና ትኩረት ተሰጥቶ የተሰራበትን ሂደት ማስቀጠል የሚችል የድህረ ምርጫ እቅድ አቅርበዋል።
ከመድረኩም በምርጫ ሂደቱ የነበሩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠል እንደሚገባና የነበሩ ክፍተቶችን ማረምና በቀጣይ በድህረ ምርጫ ሂደት በትኩረት መስራት እንደሚጠበቅና ለዚህም ዝግጁነታቸውን አንስተዋል።
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ለሁሉም!
ለሰላምና ጸጥታ መረጃዎች፦
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f97