ፀጥታ ሊረጋገጥ የሚችለው በፀጥታ መዋቅሩ ብቻ ሳ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ፀጥታ ሊረጋገጥ የሚችለው በፀጥታ መዋቅሩ ብቻ ሳይሆን ህዝቡ ባለቤት በመሆን ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል ሲችል ነው።

ፀጥታ ሊረጋገጥ የሚችለው በፀጥታ መዋቅሩ ብቻ ሳይሆን ህዝቡ ባለቤት በመሆን ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል ሲችል ነው። 

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ 

"ምርጫን ተከትሎ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ቀድሞ በመከላከል ረገድ የህዝቡ ሚና " በሚል መሪ ሀሳብ   ከ11ዱም ክ/ከተሞች ከተውጣጡ  የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

ሌተናል ጀነራል አስራት ደኔሮ  የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ በመድረኩ ተገኝተው  እንደገለፁት  ለፀጥታና ለደህንነት ስራ ትልቁ  አቅም  ህዝብ መሆኑን አንስተው ነዋሪው በየአካባቢው ያለውን የፀጥታ ሁኔታን በትኩረት በመከታተልና የወንጀል ድርጊት ሲያጋጥም ለፀጥታ አካል መረጃ በማድረስ የከተማን ሰላም ማረጋገጥ የድርሻውን መወጣት  እንደሚገባ አስገንዝበዋል። 

ጀኔራሉ አክለውም ቀጣይ በሚካሄደው 7ኛ ሀገራዊ  ምርጫን ተከትሎ ሊከሰቱ የሚችሉ የወንጀል ድርጊቶችን ቀድሞ በመከላከል እንዲሁም የሚያጋጥሙ የፀጥታ ችግሮች ላይ ለፀጥታ መዋቅሩ ጥቆማ መስጠትና ምርጫው ፍፁም ሰላማዊ  ሆኖ እንዲያልፍ በንቃት መከታተል እንደሚጠበቅ አሳስበዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ  እንደተናገሩት  የከተማን ሰላም በማስጠበቅ ረገድ የህዝቡ ሚና የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ነው ብለው  7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ  ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲያልፍና ህብረተሰቡ የሚፈልገውን መምረጥ እንዲችል ብሎክን መሰረት ያደረገ የፀጥታ ስምሪት በመስጠትና ምንም አይነት የፀጥታ መደፍረስ እንዳይኖር ከወትሮው በላቀ መልኩ ህዝቡ ተሳትፎውን መቀጠል ይገባል ብለው  ከተማችን አዲስ አበባ  በህዝቦቿ  ተሳትፎ ሰላሟ የተረጋገጠባት የማድረግ ስራ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል አብራርተዋል።

የወንጀል ጉዳትን ለመቀነስና ለማስቀረት ፣ የዜጎችን ሕይወትና ንብረት ለመጠበቅ ሰላምና መረጋጋት በማስፈን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች እንዳይጣሱ ለማድረግና አጠቃላይ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ ለማንቀሳቀስ ወንጀል መከላከል አስፈላጊ እንደሆነ አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊ በሪፖርቱ አብራርተዋል።

የተለያዩ የፀረ-ሰላም ሀይሎች በሀገራችን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሽፋን ተደርጎ የሚፈጸሙ የወንጀል ቁጥር ለመፈጸም የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለመከላከል የህዝቡ ሚና ወሳኝ መሆኑ ጠቅሰው ፣ ወንጀል አስከፊ ጉዳቶችን ከማስከተሉ በፊት መከላከል እንደሚገባ አቶ ተስፋዬ አክለው ገልፀዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም  ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው ሀገርን ሰላም ማድረግ መሆኑን ጠቁመው አሁን በከተማችን የሚታየው ፍፁም ሰላማዊ  እንቅስቃሴን ማስቀጠልና ህዝቡ የሰላም ባለቤት በመሆን በቀጣይ  7ተኛው  ሀገራዊ  ምርጫ  ያለምንም የፀጥታ ስጋትና ወንጀልን በመከላከል ረገድ የድርሻውን እንደሚወጣ ገልፀው የከተማን የሰላም ደሴትነቷን ለማስቀጠል ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ገልፀዋል። 

በመጨረሻም ህብረተሰቡ በየአካባቢው የሚያጋጥሙ የፀጥታ ስጋትና የወንጀል ድርጊት ሲያጋጥም ለአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በነፃ የስልክ መስመር 8882 ጥቆማ መስጠትና ለአዲስ አበባ ፖሊስ   991 ጥቆማና መረጃ ማድረስ እንደሚችል ተጠቁሟል።

ግንቦት 13/2018 ዓ.ም (PSAB)

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም!!!

ለፀጥታ መረጃ:--

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79