ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የተገልጋዮች እርካታ ማረጋገጥ ችሏል።
ቢሮው አገልግሎት አሰጣጡን በማሻሻል የተገልጋዮች እርካታ ማረጋገጥ ችሏል።
ግንቦት 12/2018ዓ.ም(አዲስ አበባ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አገልግሎትን በማዘመንና የተገልጋይን እርካታ ከፍ ለማድረግ ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በማበልፀግ ህብረተሰቡ ያለምንም እንግልት ከሰላም፣ ከፀጥታ፣ ከወንጀል መከላከልና ከደህንነት አንፃር በተያዘው በጀት ዓመት ባለፉት ወራቶች ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ገለጿል።
አቶ ጌታሁን አበራ የቢሮው አማካሪ እንደተናገሩት ቢሮው በትኩረት ከሚሰራቸው ስራዎች በዋናነት የከተማውን ነዋሪ ሰላም ደህንነት ማስጠበቅ ፣የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ሲሆን ከዚሁ ጋር በተያያዘም አገልግሎቶችን ማዘመንና በቴክኖሎጂ መስጠት ሌላው የትኩረት መስክ ነው ብለዋል።
አክለውም ቢሮው በአራት ዘርፍ የሚሰጠውን አገልግሎቶችን በተቀላጠፈና ዘመነ ቴክኖሎጂ እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመው በዚህም በየአካባቢው የወንጀል ምጣኔ መቀነስ መቻሉን አንስተው በቀጣይም አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አብራርተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የስታንዳርዳይዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምፀሐይ ማሞ ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን፣በገለጻቸውም የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱ የቢሮውን አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ የሚያስችል የንቅናቄ መድረክ መፍጠር መቻሉን፣ከአገልግሎት አሰጣጥ እና ብልሹ አሰራሮች አኳያ የተሰሩ ስራዎችን እና የመጡ ለውጦች በተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦች በብሮሸር በዜና በዌብሳይት ፣ በፕሮዳክሽን በመሳሰሉ ሚዲያዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ፣ግልፀኝነት ተጠያቂነት እና አሳታፊነት ስርዓትን በማጎልበት የቢሮ ተገልጋዮችን የአገልግሎት ጥያቄ እርካታ ከፍ እንዲል ማድረግ መቻሉን በሪፖርቱ አብራርተዋል።
ወ/ሮ አለምፀሐይ አክለውም ተቋሙ የሚሰጡ አገልግሎቶች እና የተገልጋይ ቅድመ ሁኔታዎች ለተገልጋይ ግልጽ ማድረግ፣በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ በስፋት ማሳወቅ፣የተገልጋይ ቅሬታና ጥቆማ በመቀበል ወቅታዊ ምላሽ መስጠት፣ተቋማዊ የአሰራር ስርዓት ለመዘርጋትና የሰላም ዕሴት ለመገንባት ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን በተገቢው ማሳደግ፣ወንጀሎችን ለመከላከል፣እርምጃ ለመውሰድና ለማስወሰድ ወደ ተግባር መግባት ቀጣይ የትኩረት በመስጠት እንደሚሰራበትም አስቀምጠዋል።
ተሳታፊዎችም የሚሰጡ አገልግሎቶች በቴክኖሎጂ መሆናቸው ከደህንነትና ወንጀል ከመቀነስ አንፃር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የ2018በጀት ዓመት ባለፉት የዘጠኝ ወራት የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሸያ የተሰሩ ስራዎችንና መስተካከል ስለሚገባቸው ጉዳዮች ከአስራንዱም ክ/ከተሞች የተወጣጡ ከህብረተሰብ ክፍሎች የጋራ ገምግሟል።
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም!!!
ለፀጥታ መረጃ:--
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79