ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ የፀጥታና የደህንነት ስራ በቴክኖሎጂ በመታገዝ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።
ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ የፀጥታና የደህንነት ስራ በቴክኖሎጂ በመታገዝ በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተገለፀ።
ግንቦት 12/2018 ዓ.ም (PSAB)
የከተማን ሰላም ማስጠበቅና ወንጀልን በመከላከል ረገድ ከህብረተሰቡ የሚነሱ ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በቴክኖሎጂ በታገዘ መልኩ ተግባራትን አስተሳስሮ እየሰራና በዚህም ተጨባጭ ውጤት እያመጣ መሆኑ ተገለፀ።
አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ እንደገለፁት የከተማን ሰላም ለማረጋገጥና የወንጀል ድርጊቶችን ለመቀነስ ቢሮው የሰላም ባለቤት ህዝብን በማድረግ ውጤታማ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን ከአዋኪ ድርጊቶች ፣ ከኦፕሬሽንና ከሰላም እሴት ግንባታ አኳያ ውጤታማ ስራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል።
ቢሮው በተያዘው በጀት ዓመት የሚሰጠውን አገልግሎቶች በተለይም የከተማን ሰላም በማስጠበቅ ሂደት ፣ በወንጀል መከላከልና የህብረተሰቡን በሰላም ወጥቶ እንዲገባ በርካታ ተግባራትን በቴክኖሎጂ እየሰጠ እንደሚገኝና የከተማውን ነዋሪዎች ያለምንም የፀጥታ ስጋት መንቀሳቀስ እንዲችል ማድረግ መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ አቶ ገብሬ ዳኘው ገልፀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ የተዋቀረው ኮሚቴ በቢሮው ከህብረተሰቡ የተነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ የሰጠበትንና አገልግሎቱን ያስተካከለበትን ሂደት ሱፐርቪዥን ያደረገ ሲሆን የተሰራበትን መንገድ በመረጃ በተደገፈ መመልከት ችለዋል።
ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም!!!
ለፀጥታ መረጃ:--
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79