የቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የቀጣይ ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን ለግልና ለመንግስት ተቋማት ጥበቃ አባላት ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተገለፀ።

የቀጣይ ሀገራዊ  ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን ለግልና ለመንግስት ተቋማት ጥበቃ አባላት ስልጠና ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተገለፀ።

ግንቦት 10/2018 ዓ.ም  (PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከፌደራልና ከአዲስ አበባ ፓሊስ ጋር በጋራ በመሆን   በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም  የቀጣይ ሀገራዊ  ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት  አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረገ ይገኛል።

 ለዚህም ለመደበኛ የፀጥታ አካሉ አጋዥ እንዲሆኑ  የግልና የቅጥር ጥበቃ ኤጀንሲዎች  ፣ የሞተር ማህበር አባላት ፣ለማህበርና ለጋራ መኖሪያ ቤት ጥበቃዎች በፀጥታ አጠባበቅና  በወንጀል መከላከል ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና  መስጠት የሚያስችል ኦሬንቴሽን ለፀጥታ አካላትና ለዘርፉ አስተባባሪዎች ተሰጥቷል።

ስልጠናው በተያዘው ሳምንት መጨረሻ እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም!!!

ለፀጥታ መረጃዎች ለማገኘት  :-
 https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79