"ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግና የጸጥታ ተቋ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግና የጸጥታ ተቋማትን በማቀናጀት በተከናወነው የሰላምና ደህንነት ስራ በሸገርና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮች ዘላቂ ሰላምን ማስፈንና በርካታ ወንጀልና ወንጀል ነክ ክስተቶችን መከላከልና መቆጣጠር ችለናል"

"ህዝብን የሰላም ባለቤት በማድረግና የጸጥታ ተቋማትን በማቀናጀት በተከናወነው የሰላምና ደህንነት ስራ በሸገርና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮች ዘላቂ ሰላምን ማስፈንና በርካታ ወንጀልና ወንጀል ነክ ክስተቶችን መከላከልና መቆጣጠር ችለናል"

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ 

ግንቦት 11/2018 ዓ.ም  (PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በከተማው ላይ አስተማማኝ ሰላም እንዲሰፋን በዋናነት ትኩረት ሰቶ እየሰራ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የጸጥታ ስራው አመርቂ ውጤት እያስመዘገበ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጋር ባለፉት ዘጠኝ ወራት በጋራ የሰሯቸውን ስራዎችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን አስመልክተው የጋራ ውይይት መድረክ አድርገዋል።

ሌተናል ጀነራል አስራት ደኔሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ እንዳሉት የአዲስ አበባ ከተማ  ከሸገር ከተማ ጋር በፀጥታና ወንጀል መከላከል ዙሪያ ከሚመለከታቸው  አጋር አካላት ጋር በቅንጅት በመሆን  ባለፉት  ጊዚያቶች  የተሰሩ  ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውንና በዚህም ከተማችን በአለምአቀፍ  ደረጃ  ተመራጭ ከተማ መሆን መቻሏን አንስተው በቀጣይ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲያልፍ በበለጠ በመቀራረብና ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤትና የመረጃ ምንጭ  ማድረግ ለላቀ ውጤታማነት መስራት  እንደሚገባ አሳስበዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ እንዳሉት  ባለፍት ዘጠኝ ወራት በተለይ ደግሞ በሁለቱም ከተሞች ላይ ሰላም የተረጋገጠበት የደህንነት ስጋት የሌለበት ህብረተሰቡ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት ከተማን መፍጠር ችለናል ያሉ ሲሆን  አያይዘውም  የጸጥታ ስራ ድንበር የለሽ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በጋራ ሰላምን በማስጠበቅ ህገ ወጥነትን በመቆጣጠር የልማትን እንቅስቃሴዎች በማፋጠን ሰላምን በማጽናት ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና በማሳተፍ የጋራ የሆነውን ሰላም ማስፈን መቻሉን ገልፀዋል።

ቢሮ ሀላፊዋ አክለውም አደረጃጀቶችን በማጠናከር  ህዝቡን ከጸጥታው መዋቅር ጋር በማቀናጀት ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ግንባታዎች ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን መከላከልና መቆጣጠር በተጨማሪ የጠላትን ሀይሎች  ሴራ የማክሸፍ የወንጀል ምጣኔዎችን በእጥፍ የቀነሰበት ሁኔታ መኖሩንና  አንዳንድ  የተለያዩ ሁኔታዎችን  ምክንያት በማድረግ የኢኮኖሚ አሻጥር በማድረግ ህብረተሰቡን ምሬት ውስጥ ለማስገባት የሞከሩ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ የመውሰድ ድንገተኛና አደጋዎችንም መቆጣጠር የተቻለበት ሂደት እንደነበርም አብራርተዋል።

የሸገር ከተማ  ም/ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ  አቶ ጉዩ ገልገሎ እንዳሉት ሁለቱም ከተሞች በጋራ በመስራታቸው በተለይ  ከጸጥታ አንጸር አመርቂ ውጤት  እየታየ በመምጣቱ  ህብረተሰቡ ሰላሙ የተጠበቀ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

 ኃላፊው አክለውም ቀድሙ  የነበረውን ቅንጅታዊ አሰራር  በማጠናከር በጋራ የሀገራችንን ዕድገት በማፍጠን ሰላም እንዲሰፍን በበለጠ ተጠናክሮ ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።

ሁለቱ ከተሞች የኢንቨስትመንትና የልማት ማእከል እንዲሆኑም ቅንጅታዊው የጸጥታ አስተዳደር ስራ አበርክቶው የላቀ መሆኑንም ተነግሯል። 

በከተሞቹ የጋራ ቅንጅታዊ ስራዎችም ከተማ አቀፍ ሁነቶች ሀይማኖታዊና ባህላዊ የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዳለፉ ሁሉ የመጣውንም ውጤት በተሻለ መልኩ አጠናክሮ በማስቀጠል መጭሙ 
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊና ፍትህአዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅም ቅንጅታዊ ስራዉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የቀጣይ  አቅጣጫ  ተቀምጧል።

በውይይቱ ላይ የሁለቱም ከተማ የሰላም ጸጥታ አስተዳደር ሀላፊዎች፣የንግድ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የገቢ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የፖሊስ መምሪያ አዛዦች፣የደንብ ማስከበርና የሚሊሻ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣እሳትና ድንገተኛ አደጋ ኮሚሽን ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ሰላም ከሁሉም፣ በሁሉም፣ ለሁሉም!!!

ለፀጥታ መረጃዎች ለማገኘት  :-
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79