" ለተቋም ግንባታ ውጤታማነት በዘርፉ ያሉ አመራር እና ሰራተኞችን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት ወሳኝ ነው"።
" ለተቋም ግንባታ ውጤታማነት በዘርፉ ያሉ አመራር እና ሰራተኞችን የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን መስጠት ወሳኝ ነው"።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ
ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
ግንቦት 10/09/2018ዓ.ም ( PSAB)
በሁለት ዙር ሲሰጥ የነበረው ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት የማጠቃለያና የዕውቅና መድረክ ተካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር፣ ከማዕከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች በሁለት ዙር ሲሰጥ የቆየው የንድፈ ሐሳብና የአካል ብቃት ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቆ፣ የማጠቃለያና የዕውቅና መድረክ ተካሄደ።
በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የአመራር ብቃት ፣ ሙያዊ ክህሎትና የአካል ዝግጁነት ከማጠናከር ባሻገር ፣ በቀጣይም ለከተማዋ ሰላምና ፀጥታ ስራዎች ውጤታማነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው እና በጠንካራ የተቋም ግንባታ ለተገልጋይ ጥረት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚችል፣አሰራርንና ቴክኖሎጂን የማቀናጀት ጥበብ እና በሳይንሳዊ መንገድ የሰው ሀይል መገንባት ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናም ሰጥተዋል።
ሀላፊዋ አክለውም ስልጠናው በአመራር አቅም ግንባታና በተቋማዊ አፈጻጸም ማሻሸያ ላይ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት አንስተው፣ተቋምን ጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባት የተቋም ራዕይ፣ተልዕኮና ዕሴት፣የሰው ሀይል ልማት፣መዋቅርና አሰራር ላይ እና የተቋም ባህል መሠረት በማድረግ የተቋሙን ግንባታ መገንባት እንደሚቻልም ጠቁሟል።
በመድረኩ ማጠቃለያ የተሰጠው ስልጠና መነሻ በማድረግ ራስን በማንበብ ማብቃት ፣ ከወቅቱ ጋራ አብሮ መራመድ ፣በስልጠና የተገኙ አቅም ወደ ተግባር መቀየርጨ ፣ የፀጥታ ስራ በቴክኖሎጂ ለማስደገፍ በከተማ የለሙ ቴክኖሎጂዎች ወደ ክ/ከተማና ወረዳ ማውረድ፣ህብረተሰቡ እንዲጠቀበምባቸው ግንዛቤ ከመፍጠር ጀምሮ አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እና 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን መደበኛና አጋዥ የፀጥታ ሀይሎችና ህዝቡን በማስተባበር በትጋት መስራትና ማሰራት ፣ ከተቋሙ እይታ ውጪ የሚሆን አንዳንች የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር በንቃት በቅንጅት መስራት ይገባል ሲሉ የቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በመጨረሻም የማጠቃለያና የዕውቅና ፕሮግራም ተሰጥቶ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79