የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ያሰለጠናቸውን 12,800 የሚሆኑ 7ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና  ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  ያሰለጠናቸውን 12,800  የሚሆኑ 7ኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላት በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።

        ግንቦት 09/2018 ዓ.ም(PSAB)
                     ****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ   በንድፈ ሐሳብና በመስክ ወታደራዊ ስልጠና  ያሰለጠናቸውን 7ኛው ኮርስ አዲስ ምልምል የሠላም ሠራዊት አባላትን  በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል።

በዕለቱ  መረሃ ግብሩ ላይ በመገኘት መልክት ያስተላለፉት ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ  የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላይ አዛዥ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት የ7ኛ ዙር ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን በንድፈ ሃሳብና አካላዊ ብቃት በማሰልጠኑ በአመለካከትና በአካል ብቃት በመብቃታቸው በአዲስ አበበ ፖሊስ ስም በማመስገን፤የአዲስ አበባ ፖሊስና የሰላም ሰራዊት እጅ ለእጅ በመያያዝ የጸጥታዉ ስራ የተሳካ እንዲሆንና 7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ በቅንጅት የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል።

በምርቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዉ መልእክት ያስተላለፉት አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ በንግግራቸው አሁን እንደ ሀገር ያለንበት ምእራፍ በእምርታ እያንሰራራን ያለንበት ወቅትና በከተማችን ተጨባጭና አስገራሚ ለዉጦች በአጭር ጊዜ የተመዘገበው  ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና መደበኛውን የጸጥታ ሀይል ከሰላም ሰራዊቱ ጋር በቅንጅት ሰፊ ስራ እንዲሰራ በመደረጉ ነዉ ሲሉ ተደምጠዋል።

የአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ  ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በበኩላቸው  በአዲስ አበባ ከተማ የተጀመረው የማያቋርጥ ልማትና ለዉጥ የተሳለጠ እንዲሆን አስተተማማኝ ሰላም ወሳኝ ነዉ በማለት፤የከተማዉን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የህዝቡን የሰላም ባለቤትነት በሚያጎላ መልኩ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተሠሩ ስለመሆኑ አዉስተዋል።

ሀላፊዋ አክለዉም  አዲስ ተመራቂ የሰላም ሰራዊት አባላት ከነባሩ የሰላም ሰራዊት አባላት ጋር ተቀናጅተው  የአካባቢያቸውን የከተማቸዉን ሰላም እየጠበቁ ይገኛሉ ያሉ ሲሆን በርካታ የፌደራልና የአዲስ አበባ የፖሊስ አባሎች ፣የደንብ ማስከበር ኦፊሰሮችና የዛሬ ተመራቂዎችን ጨምሮ ከ200,000 በላይ የሰላም ሰራዊት አበላት ሌሎች የጸጥታ የፀጥታ አጋዥ ኃይሎች  ህብረተሰቡን የሰላሙ ባለቤት በማድረግ የከተማዉን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ሌት ተቀን በቅንጅት እየሠሩ እንደሚገኙ አበክረው የገለጹ ሲሆን፤     በዛሬው ዕለትም ከ12ሺህ በላይ አዲስ የሰላም ሰራዊት  ምልምል  ማስመረቁንና በቀጣይ በሀገሪቷ  7ኛዉ ሀገራዊ ምርጫ ከጸጥታ አኳያ ምርጫዉ ፍጹም  እንዲሆን ህዝቡ የሠላም ጋሻና መከታ እንዲሆን መላዉ የጸጥታ መዋቅሩ ከበቂ በላይ ዝግጅት ማድረጉን አረጋግጠዋል።

ስልጠናውን ላጠናቀቁ አዲስ የሰላም ሰራዊት አባላትና ስልጠናውን ሲሰጡ ለነበሩ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አባላት  የዕውቅና የምስክር ወረቀትና የዋንጫ ስጦታ ተበርክቷል።

በመርሃ-ግብሩ ላይ ሌ/ጀነራል አስራት ደኔሮ  የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላይ አዛዥ ፣አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በምክትል ከንቲባ ማእረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ፣ የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ዋና ሥራ አስኪያጅና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች የማዕከል ምክትል ቢሮ ሀላፊዎችና የየ ክፍለ ከተማዉና የየወረዳዉ ሰላምና ጸጥታ ጽ/ቤት ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79