የሰላም ሰራዊት ለአካባቢው ሰላምና ደህንነት ዘብ የቆመ ነው!
የሰላም ሰራዊት ለአካባቢው ሰላምና ደህንነት ዘብ የቆመ ነው!
አካባቢን በንቃት በመጠበቅ የከተማን ደህንነት የማረጋገጥ ስራ በከተማችን አዲስ አበባ በህዝቦች ተሳትፎ በተጠናከረ መልኩ ቀጥሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማዋን ነዋሪዎች ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የጸጥታ አካላት እና የሰላም ሰራዊት የተቀናጀ የአንድ ማዕከል ስምሪት እየሰጠ ይገኛል።
በዚህም ህዝቡን ያሳተፈ የፀጥታና የወንጀል መከላከል ሰራ እየሰራና ከተማዋ የጀመረችውን የለውጥ ግስጋሴ እያስቀጠለ ከመሆኑ ባሻገር መጭው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን በንቃት እየሰራ ይገኛል።
የቢሮው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችም በአንድ መአከል የሰላም ሰራዊትና የፀጥታ አካላት ስምሪት ላይ ተገኝተው ስምሪት ሰጥተዋል።
ግንቦት 7/2018 ዓ.ም (PSAB)
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79