የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላም ዘላቂ ለማድረ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከኢፐሰዩ ጋር በመሆን የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ትስስር መድረክ አከናወነ።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ  የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከኢፐሰዩ ጋር በመሆን የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ትስስር መድረክ አከናወነ።
            **
ግንቦት 07 ቀን 2018 ዓ/ም (PSAB)

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ አስተማማኝና ስጋት የሌለበት የካምፓስ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል፤ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት የተማሪዎችን ሁለንተናዊ ደህንነት የሚጠብቅ ታሪካዊ የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ትስስር መድረክ አካሄደ።

ቢሮው ማህበረሰቡን በማሳተፍ የከተማዋን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል አንዱ በሆነው በዚህ መርሃ-ግብር፤ “የቤተሰብ ትስስር ለተማሪዎች ውጤማነት” በሚል መሪ-ቃል ከቤተሰቦቻቸው ርቀው ለሚማሩ ለጋ ወጣት ተማሪዎች በአካባቢው ነዋሪዎች አማካኝነት ማህበራዊ፣ ስነ-ልቦናዊና አካዳሚኪያዊ ድጋፍ የሚደረግበት የቃል-ኪዳን ፊርማ በዩኒቨርሲቲው አባይ አዳራሽ በደማቅ ሁኔታ የፊርማ ስነስርአት ተካሂዷል ።

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት የቢሮውን ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ የገለጹት የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን እንየው ባደረጉት ንግግር፤ የቃል-ኪዳን ቤተሰብ ትስስሩ የተማሪዎችን ግላዊና አካዳሚያዊ ችግሮች ከመፍታት ባለፈ፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ሊፈጠሩ የሚችሉ የፀጥታ ስጋቶችን ቀድሞ ለመከላከልና በሀገር ደረጃ ሰላምና አንድነትን ዘላቂ ለማድረግ የሚኖረው ፋይዳ እጅግ የጎላ ስለመሆኑ አስታዉሰዉ ቢሮዉ ለዚህ ስኬት ከአካባቢው ማህበረሰብና ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ያለውን ቅንጅት አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ንጉስ ታደሰ በበኩላቸው፣ ተማሪዎች ቀላሉን ችግራቸውን የሚረዳላቸው አካል በማጣት ለተለያዩ ማህበራዊ ተጋላጭነቶችና ለውጤት ዝቅተኝነት እንዳይዳረጉ ይህ የቤተሰብ ትስስር ትልቅ ክፍተት እንደሚሞላ ገልጸው፣ የሰላምና ጸጥታ ቢሮው ለካምፓስ ሰላምና ለተማሪዎች ደህንነት ለሰጠው ከፍተኛ ትኩረት አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተሸመ ዱላ በመዝጊያ ንግግራቸው፣ ይህ መድረክ ሰላማዊ የሆነ ካምፓስ ከመፍጠር ባሻገር፣ ሀገር የምትጸናበት እና የምትኮራበት ኢትዮጵዊ ስሜት የሚገነባበት ብሄራዊ ምሰሶ የተተከለበት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።

በመድረኩ ላይ ከሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የተወከሉ የሃይማኖት አባቶች ተገኝተው ቃለ ቡራኬና ጸሎት ያደረጉ ሲሆን፣ ከአካባቢው ማህበረሰብ ከተወጣጡ ግለሰቦች ጋር የተማሪዎችን ደህንነት በኃላፊነት ለመጠበቅ የሚያስችል የቃል-ኪዳን ፊርማ ተፈርሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሙዚቃ ባንድም በመርሃ-ግብሩ ላይ ተገኝቶ፣ ልዩ ልዩ የብሄር ብሄረሰቦች ባህላዊ ውዝዋዜዎችንና ዘመናዊ ሙዚቃዎችን በማቅረብ ለዕለቱ መድረክ ልዩ ድምቀት ሰጥቶታል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79