"ወንጀል በመከላከል እና ሰላማዊ ምርጫ በማድረግ ረገድ የህዝቡ ሚና " በሚል ርዕስ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
"ወንጀል በመከላከል እና ሰላማዊ ምርጫ በማድረግ ረገድ የህዝቡ ሚና " በሚል ርዕስ ህዝባዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ።
ግንቦት 6/2018 ዓ.ም (PSAB)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በኩል ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን የሰላም ባለቤት ህዝቡን በማድረግ ወንጀል በመከላከል እና ሰላማዊ ምርጫ በማድረግ ረገድ የህዝቡ ሚና ምን መምሰል አለበት በሚል ርዕሰ በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የሀይማኖት አባቶች ፣ የፀጥታ አካላትና ነዋሪዎች በተገኙበት ውይይት አካሂዷል።
አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ በአዲስ አበባ ከተማ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት በሀገራችን ብሎም በከተማችን እየተሰሩ በሚገኙ የለውጥ ስራዎች አዲስ አበባ የስበት ማዕከል እየሆነች መምጣቷን አንስተው ይህን የተጀመሩ የለውጥ የልማት ስራዎችና ቱርፋቶችን ለማስቀጠልና 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ነፃ ፍትሀዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲያልፍና ህብረተሰቡ ይበጀኛል የሚለውን መንግስት የሚሆነውን ፓርቲ ለመምረጥ እንዲችል የከተማችንን ሰላም ማስጠበቅና ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ኃላፊው አክለውም የከተማን ሰላም ለማወክ የሚሞክሩና የወንጀል ድርጊቶችን የሚፈፅሙ ፀረ ሰላሞችን በመመከትና ወንጀልን በመከላከልና ወንጀለኞችን በማጋለጥ ህብረተሰቡ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል።
ዶ/ር ደበሌ ቃበታ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮምሽን ኮምሽነር እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ከተማ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ረጋ ብሎ በማሰብና በመመልከት የሰላም ፊትአውራሪነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለው ምንም አይነት ወንጀል እንዳይፈፀም ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካሉ ጎን በመሆንና ከፊታችን ያለውን ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን በትኩረት ነገሮችን መመልከት ይገባል ብለዋል።
አቶ አድማሱ ደቻሳ የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ እንዳሉት በሀገራችን ከለውጡ ማግስት ጀምሮ የተሰሩና እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎችን በውጤታማነት ለማስቀጠል የከተማን ሰላም ማረጋገጥና ወንጀልን መጠየፍ ቀዳሚ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ወንጀል በመከላከል እና ሰላማዊ ምርጫ በማድረግ ረገድ የህዝቡ ሚና በሚል ርዕስ የመወያያ ሰነድ በለሚኩራ ክ/ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አየለ ተስፋዬ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
መድረኩ በሁሉም ክ/ከተሞች እየተካሄደ ይገኛል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79