በ7ተኛው ዙር የሰላም ሰራዊት ስልጠና ላይ እየተ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በ7ተኛው ዙር የሰላም ሰራዊት ስልጠና ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሰልጠኞች በመስክ ልምምዳቸው ለሰላም ማስጠበቅ ብቁ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናገሩ።

በ7ተኛው ዙር የሰላም ሰራዊት ስልጠና ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሰልጠኞች በመስክ ልምምዳቸው ለሰላም ማስጠበቅ ብቁ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናገሩ።

ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማዋን ሰላም የማስጠበቅና የወንጀል መከላከል ሂደት ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ ሲሆን ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ በበጎ ፈቃደኞች   7ተኛ ኮርስ አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት  እየሰጠ ያለውን  ስልጠና የመስክ የስልጠና ሂደቱን  ምልከታ አድርጓል።

ስልጠናውን እየወሰዱ የሚገኙ አዲስ የሰላም ሰራዊት አባላቱም በመስክ ወታደራዊ ልምምዳቸው የከተማን ሰላምና ደህንነት  ማስጠበቅ ላይ ብቁ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ  ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ የፀጥታና የደህንነት ስራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑንና በዚህም  በከተማዋ የወንጀል ምጣኔ እየቀነ መሆኑን ገልፀዋል።

ኃላፊው አክለውም   በተያዘው  በጀት ዓመት ብቻ 33 ሺህ የሰላም ሰራዊት ሰልጥነው  ወደ ስራ መግባታቸውን አውስተው   በሁሉም ክ/ከተሞች 7ተኛው ኮርስ  አዲስ የሰላም ሰራዊት ምልመል   ከ12,800  በላይ ስልጠናውን እየወሰዱ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

 ዛሬ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በመገኘት  የ7ተኛው ዙር አዲስ የሰላም ሰራዊት  የመስክ ወታደራዊ ስልጠናን ተመልክተው ሰልጣኞቹን አበረታተዋል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79