" በጎነት ለጋራ መግባባትና በአብሮነት ሀገርን...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

" በጎነት ለጋራ መግባባትና በአብሮነት ሀገርን ለማልማት ጉልህ ድርሻ አለው " አቶ ብርሃኑ ረታ

" በጎነት ለጋራ መግባባትና  በአብሮነት ሀገርን ለማልማት ጉልህ ድርሻ አለው "

 አቶ ብርሃኑ ረታ 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሃይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ 

           ***
ግንቦት 04/2018 ዓ.ም (PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ፤ 14ኛው ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ወጣት አምባሳደሮች በከተማዋ በነበራቸው የቆይታ ጊዜ ያከናወኗቸውን ተግባራትና የስራ አፈጻጸምን  ገመገመ።

አቶ ብርሃኑ ረታ  የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ኃላፊና የሃይማኖትና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ በግምገማ መድረኩ መክፈቻ ላይ እንዳሉት በጎነት ለጋራ መግባባትና  በአብሮነት ሀገርን ለማልማት ጉልህ ድርሻ አለው   ብለው  ወጣቶቹ  በበጎ ፈቃድ  ያከናወኑትን ተግባር የሚበረታታ ነው ብለዋል።

ሀላፊዉ በንግግራቸው ከምንም በላይ ሰው ሆኖ መቆም የሚቻልበትን የጋራ ዕድል መፍጠር ትልቁ ስኬታችን ነው በማለት ሁላችንም በጋራ የምንወዳትን ሀገራችንን ማልማት የምንችለው በአብሮነት ስንቆም ብቻ ሲሆን እኛ ኢትዮጵያውያን የቋንቋ፣ የሃይማኖትና የባህል ብዝሃነታችንን እንደ ፀጋ በመቁጠር በጥብቅ የተጋመደ ትስስር ስላለን በጎ ፈቃደኛ ወጣቶቹ  ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የመጡ እንደመሆናቸው  የብዝሃነትና የባህል ልውውጥ እሴት በአዲስ አበባ ቆይታቸው በተግባር በማሳየታችሁ ክብር ይገባችኋል ሲሉም ተደምጠዋል። 

አቶ ብርሃኑ አክለውም ለዚህ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉትን በየደረጃው ያሉ አመራሮችን አመስግነዋል።

በመቀጠልም የቢሮው የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን እንየው፤ የበጎ ፈቃደኞቹን የቆይታ ጊዜ ዝርዝር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በሰነድ መልክ አቅርበዋል። በቀረበው ሪፖርት ላይም ከተሳታፊዎች ሰፊ ሀሳብና አስተያየት ተነስቶ ገንቢ ውይይት ተካሂዶበታል።

በግምገማ መድረኩ ላይ ወጣት አምባሳደሮቹ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ያገኙትን ልምድ፣ ያዳበሩትን የሰላም እሴትና ተሞክሮ ለተሳታፊዎች ያካፈሉ ሲሆን፤ በቀጣይም በየሄዱበት አካባቢ የሰላም አምባሳደር በመሆን እንደሚያገለግሉ ተናግረዋል ።

በመጨረሻም ለወጣት በጎ ፈቃደኞቹ ላበረከቱት ጉልህ አስተዋጽኦ የእውቅና ሰርተፊኬት በመስጠት መርሃ-ግብሩ በስኬት ተጠናቋል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79