የፓርኪንግ ማህበራት ለከተማዋ ሰላም መጠበቅ ት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የፓርኪንግ ማህበራት ለከተማዋ ሰላም መጠበቅ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ ።

የፓርኪንግ ማህበራት ለከተማዋ ሰላም መጠበቅ  ትልቅ ሚና እንዳላቸው ተገለፀ ።
       **
ሚያዚያ 30/2018 ዓ.ም (PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ፤ በከተማዋ ለተደራጁ የፓርኪንግ ማህበር አባላትና አመራሮች በወንጀል መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ። ስልጠናው የፓርኪንግ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው ላይ ሆነው ለጸጥታ መዋቅሩ አጋዥ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ እንደሆነም በመድረኩ ተገልጿል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ምክትል ኃላፊና የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር፤ ሰላም ከሌለ ነገን ተስፋ አድርጎ መኖር እንደማይቻል ገልጸው፣ የከተማዋን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ የመንግስት ብቻ ሳይሆን የሁሉም ዜጋ ኃላፊነት መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል።

ኃላፊው አክለውም ሰላምን ለማስፈን ትብብር፣ ቅንጅትና አንድነት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ  የፓርኪንግ ማህበር አባላት በየአካባቢው ካለው የጸጥታ መዋቅር፣ ከትራፊክ ማናጅመንትና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በጋራ በመሆን የወንጀል መከላከል ስራው ላይ ትልቅ አጋዥ መሆን አለባቸው ብለዋል።

በኢንስፔክተር ፍቃዱ አቶምሳ የቀረበው የሥልጠና ሰነድ፤ የወንጀል ምንነት፣ መከላከያ ዘዴዎችና የፓርኪንግ ማህበር አመራሮችና ሰራተኞች ሊወጡት የሚገባውን ሚና በዝርዝር ዳስሷል። በተለይም አጠራጣሪ እንቅስቃሴዎችን በንቃት በመከታተልና መረጃዎችን በወቅቱ ለጸጥታ አካላት በማድረስ ረገድ የፓርኪንግ ሰራተኞች ያላቸውን አይነተኛ ሚና ሰነዱ አመላክቷል።

መድረኩን የመሩት አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ኢንጅነር ኤሊያስ ዘርጋ  የአዲስ አበባ ከተማ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና ኮምሽነር አለማየሁ  አልቄ   የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክተር ሲሆኑ ከሰልጣኞች  አስተያየት እና ጥያቄ ተነስቶ በአወያዮቹ ሰፊ ማብራሪያና ምላሽ ተሠጥቶበታል።

በመድረኩ ላይ የተሳተፉ የማህበራቱ አባላት በበኩላቸው፤ የተሰጣቸው ስልጠና በስራቸው ላይ ደህንነትን ለመጠበቅ የሚረዳቸው መሆኑን ገልጸው፣ ለከተማዋ ሰላምና ደህንነት የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤በስልጠናዉ የቢሮው ምክትል ኃላፊና የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር፣ኢንጅነር ኤሊያስ ዘርጋ  የአ/አ/ከተማ ትራፊክ ማንጀመንት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር፣ ኮምሽነር አለማየሁ  አልቄ    የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክተር እና የየ ክፍለ ከተማዉ የዘርፉ አስተባባሪዎች እና የ11ዱም ክፍለ ከተማ የፓርኪንግ ማህበር አባላት ተሳትፈዋል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79