የፀጥታና መሰል ስራዎችን በቴክኖሎጂ ማዘመንና በዲጂታል ሲስተም አገልግሎትን ተግባራዊ ማድረግ የከተማን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።
የፀጥታና መሰል ስራዎችን በቴክኖሎጂ ማዘመንና በዲጂታል ሲስተም አገልግሎትን ተግባራዊ ማድረግ የከተማን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ።
*
ሚያዚያ 29/2018 ዓ.ም (PSAB)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋና ተደራሽ ለማድረግ የጀመረውን የዲጂታላይዜሽን ጉዞ ለማፋጠን፤ ለቢሮው ዳይሬክተሮችና ለደጋፊ የሰው ኃይል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ።
ይህ ስልጠና ቢሮው እያለማቸው ያሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ እንዲገቡና የአሰራር ግልጽነትን ለመፍጠር ያለመ ነው። በመድረኩም በሰው ኃይል መረጃ አስተዳደር (ICMIS)፣እንዲሁም በፕላኒንግና ሪፖርቲንግ ሲስተም አጠቃቀም ዙሪያ ዝርዝር ስልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናዉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ገብሬ ዳኛው ቢሮው የጀመረውን የሪፎርም ስራ በማሳለጥ ረገድ የቴክኖሎጂን አስፈላጊነት ሲያብራሩ አገልግሎቱን ዘመናዊ ለማድረግ በርካታ ሲስተሞችን እያለማ እንደሚገኝ ጠቁመዉ እነዚህ ቴክኖሎጂዎች ውጤታማ የሚሆኑት አመራሮችና ፈጻሚዎች በሙሉ አቅማችን ወደ ስራ ሲቀይሩት እንደሆነ በማስታወስ ሲስተሞቹን መተግበሩ ስራን ከማቅለሉም ባለፈ ተጠያቂነትን የሚያሰፍንና መረጃዎችን በወቅቱና በጥራት ለማግኘት የሚያስችል በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ባለሙያ የቴክኖሎጂ ባለቤት ሊሆን እንደሚገባ አመላክተዋል።
በሶስት ርእሶች ላይ በተሠጠዉ ይሀዉ ስልጠና፣በሰው ኃይል መረጃ አስተዳደር (ICMIS) ፣ በፕላኒንግና ሪፖርቲንግ ሲስተምን ፣ እቅድና ሪፖርትን በዲጂታል መንገድ በማቀናጀት ስራን በቅርበት መከታተል በሚቻልበት አግባብ ላይ፤ ግንዛቤ ተሰጥቷል።
ቢሮው የፀጥታና መሰል ስራዎችን በቴክኖሎጂ ማዘመንና በዲጂታል ሲስተም አገልግሎትን ተግባራዊ እያደረገ ሲሆን ለዚህ ስራ በስሩ ያሉ ሰራተኞችን በቴክኖሎጂ ብቁ በማድረግ የከተማን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል።