በቢሮ ደረጃ የለሙ ቴክኖሎጂዎችን በሙሉ አቅም ወ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በቢሮ ደረጃ የለሙ ቴክኖሎጂዎችን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለመቀየር እንዲያመች ለሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ አስተባባሪዎች ስልጠና ተሰጠ።

በቢሮ ደረጃ የለሙ ቴክኖሎጂዎችን በሙሉ አቅም ወደ ስራ ለመቀየር እንዲያመች ለሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ አስተባባሪዎች ስልጠና ተሰጠ።

    ሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም (PSAB)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ በስሩ ለሚገኙ የየክፍለ ከተማዉ አስተባባሪና በድን መሪዎች የለሙ ሲስተሞችን አጠቃቀም አቅምን ሊገነባ የሚችል ስልጠና ሰጠ።

በስልጠናው በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ብርሃኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊና ምክትል የቢሮ ሀላፊ ሲሆኑ፤በቢሮዉ እየለሙ ያሉ ቴክኖሎጂዎች የተገልጋዩን እንግልት ለመቀነስ ያለሙ መሆናቸዉን በማዉሳት በተለይም በሀይማኖትና ሠላም እሴት ግንባታው ዘርፍ ያሉ ተገልጋዮች የእምነት ተቋማት በመሆናቸዉ በቅሬታ አቀራረብና አፈታት ስርዓት ሂደት ያለዉን መመላለስ በማስቀረት ባሉበት ሆነዉ እንድናገለግላቸዉ የለሙ ሲስተሞች በመሆናቸዉ በዘርፉ የሚሰራ ባለሙያ ቀድሞ ስለ ሲስተሙ በመገንዘብ በቀጣይ ተገልጋዮቹ በምን አግባብ ቅሬታ ማቅረብ እንደሚገባቸዉ የስልጠና መድረክ ይመቻቻልም ነዉ ያሉት።

አቶ ብርሃኑ አክለዉም ስልጠናዉ ለሁሉም ክፍለ ከተማ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች በአንድ ማእከል መደረጉ ሲስተሙ የለማበትን አላማዎች በአዝማሚያ ትንተና፣የድጋፍና ክትትል ስርዓት መተግበርና በመሠል ተግባሮች በስልጠናው ወቅት በሚኖሩ ግብረመልሶች የሁሉም ሠዉ ግብዓት ተሠብስቦ በስራ ዉስጥ እንዲዳብር ለማስቻል እንደሆነ ጠቁመዋል።

ስልጠናውን የሰጡት ከኢኖሼሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ የተገኙት አቶ ዳንኤል ተሾመ ሲሆኑ፤የ11ዱም ክፍለ ከተሞች አስተባባሪዎች በስልጠናዉ መታደም ችለዋል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79