በልማትና በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ህዝቡ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በልማትና በሰላም ግንባታ ሂደት ውስጥ ህዝቡ የእውነተኛ ሰላም ባለቤት በመሆኑ ሰላሟ የተረጋገጠባትና ልማቷ በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኝ ከተማን መገንባት ተችሏል።

በልማትና በሰላም ግንባታ  ሂደት  ውስጥ ህዝቡ የእውነተኛ ሰላም ባለቤት በመሆኑ ሰላሟ የተረጋገጠባትና ልማቷ በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኝ  ከተማን መገንባት ተችሏል።

            አቶ ተስፋዬ ደንድር 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ 

ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም 
(አ.አ.ከ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የስታንዳርዳይዜሽን አገልግሎት ዝግጅት ክትትልና ምዘና ክፍል በመልካም አስተዳደርና የቅሬታ አቤቱታ ዙሪያ በበጀት አመቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት  ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላትና ሲቪክ ማህበራት ጋር ግምገማዊ ውይይት አድርጓል።

 አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ እንደገለጹት በልማትና በሰላም ግንባታ  ሂደት  ውስጥ ህዝቡ የእውነተኛ ሰላም ባለቤት በመሆኑ ሰላሟ የተረጋገጠባትና ልማቷ በፈጣን ዕድገት ላይ የምትገኝ  ከተማን መገንባት ተችሏል ብለው  በከተማችን ጨለማን ተገን ተደርገዉ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ከመታገል አንጻር ህዝቡ ሚናዉ የጎላ መሆኑን አዉስተዉ ፤ቢሮዉ በበጀት አመቱ ከህዝብ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ምላሽ እንዲያገኝ በማለም አስቀድሞ እቅድ በማቀድና ሂደቱን የሚከታተል ባለሙያ በማሳተፍ ሰፊ ስራ ስለመሠራቱ አብራርተዋል።

አቶ ተስፋዬ አክለዉም ቢሮዉ ብቻውን የሚሰራው ስራ እንደሌለ በመገንዘብ ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላቱ ጋር በጋራ በመስራት  የመጣውን ለውጥ በከተማው ባለዉ ሰላም የሚታይ መሆኑን  በመጥቀስ  የለውጡ አንዱ ማሳየ የሆኑት በቢሮው ደረጃ የተፈቱና እየተፈቱ ለሚገኙ ቅሬታዎችና መልካም አስተዳደሮች ጥያቄዎች የባላድርሻ አካላቱምና የጎላ በመሆኑ ምስጋና አቅርበዋል። ።

ኮማንጀር ሙሉጌታ በጋሻዉ የቢሮዉ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ከውይይት  መድረኩን ከተሳታፊዎች የተነሱ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል ክፍተቶችን ደግሞ ሙሉ በሙሉ በእቅድ አካተን እንሰራለን በማለት ከህብረተሰቡ ጋር ተግባብቶ በመስራትና ቢሮው በተሰጠው ስልጣንና ሀላፊነት መሰረት እኩል አገልግሎት እየሰጠና በተገቢው መንገድ እየሰራም እንደሆነና ቢሮውን በተመለከተ ጉዳይ ሁሉ ያሉ ክፍተቶች እንደሚፈቱና ከቴክኖሎጂ ጋር በሲስተም የታገዘ ስርአት በመዘርጋት ህብረተሰቡን ይዘን በቅንጅት እንሰራለን ያሉ ሲሆን በተነሱት ጥያቄዎች ላይ ምላሽና ማብራሪያም ሰጥተዉ ከተማውን የሚመጥን አግልግሎት በመስጠትና ሰላምና ጸጥታን በማረጋገጥ ሃላፊነታችንን በጋራ እንወጣለንም ሲሉ ተደምጠዋል።

ወ/ሮ አለምጸሀይ ማሞ  ቢሮ ስታንዳርዳይዜሽን አገልግሎት ዝግጅት ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬ ዳይሬክተር በበኩላቸው ለተነሱት ሀሳብና አስተያየቶች ሰፊ ማብራሪያ የሠጡ ሲሆን የጸጥታ ጉዳይ የሀገር ጉዳይ በመሆኑ አንድነት፣ህብረት፣መተሳሰብና መቻቻል እንደሚገባ አመላክተዋል።

በ2018 ዓ.ም ባለፉት ዘጠኝ ወራት  ውስጥ በመልካም አስተዳደርና ቅሬታና አቤቱታ አፈታት ላይ የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት ያቀረቡት ወ/ሮ አለምጸሀይ ማሞ የአዲስ አበባ  ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ስታንዳርዳይዜሽን አገልግሎት ዝግጅት ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርት ላይ ከተሳታፊዎች ለቀረበው ሀሳብና አስተያየት ለአወያዮቹ ምላሽ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

በውይይቱ ላይ አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትል ፣ቢሮ ሀላፊ፣የመማክርት ጉባኤ አባላት፣የሀይማኖት አባቶች፣ከየ ክፍለ ከተማዉ የተወጣጡ ባለድርሻ አካላት፣የሲቪክ ማህበራት፣የጸጥታ አካላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል ።