"24 ሰአት የማይተኛ፤ለከተማችን ሰላምና ብልጽግ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

"24 ሰአት የማይተኛ፤ለከተማችን ሰላምና ብልጽግና የሚተጋ !!"

"24 ሰአት የማይተኛ፤ለከተማችን ሰላምና ብልጽግና የሚተጋ !!"

አዲስ አበባ ከተማን የሚመጥን የጸጥታ የደህንነት  ስራ እየተሰራ ይገኛል ።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ

ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም 
(አ.አ.ከ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ 7ኛ  ኮርስ  አዲስ ምልምል የሰላም ሰራዊት አባላትን በንድፈ ሀሳብና በመስክ ወታደራዊ ስልጠና በሁሉም ክ/ከተማች መልምሎ የስልጠናውን ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እያካሄደ  ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ማስጀመሪያ መድረክ በክብር እንግድነት የተገኙት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ በኢዲስ ከተማ ክ/ከተማ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት አዲስ አበባ ከተማ ተመራጭ ሰላሟ የተረጋገጠባት ለኑሮ ምቹ ዜጎች ደህንነታቸውን በጋራ እንዲጠብቁ ለጸጥታው መዋቅር አጋዥ የሆኑ የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ከፍተኛውን አስተዋጽኦ እየተወጣ እንደሚገኝ አስታውሰው የከተማውን ደህንነት በማስጠበቅ በኩል ተኪ ሆነው እየሰሩ የሚገኙ አካባቢውን በመጠበቅ የነቃ ተሳትፊና በወጣት ሀይልም እየተተካ የሚገኝ የሰላም ሰራዊት አባላት መኖሩን ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ  ገልፀዋል። 

ኃላፊዋ አክለውም የከተማውን  ወጣቶች ተሳትፎን በማበረታታት ዘርፍ ብዙ ስራዎች በከተማው ላይ በመሰራቱ የጸረ ሽብር ሀይሎችን ሴራ የማክሸፍ ፣  የህዝቡ ተሳትፎ የጎለበተበት ፣ ህብረተሰቡ ብሎኮችን እንዲጠብቅና  ቢሮውም በየአካባቢው ካሜራዎችን የገጠመበት፣  የጸጥታውን ወዋቅር በማጠናከር አካባቢውን የሚጠብቅ ለጸጥታው ስራ አይተኬ የሆነ ስራ በመስራትና የጸጥታ መደፍረስ እንዳያጋጥም በመስራት በኩል ሰራዊቱ ትልቁን ስፍራም እንደሚይዝ ጠቅሰዋል ።

እንደ ኃላፊዋ   ገለፃ አሁን ላይ ያለው ይህ አስተማማኝ ሰላም በቀጣይ እንዲቀጥል በተለይ የሰላም ሰራዊቱ ወጣቱ ትውልድ ሀገርን መገንባት ላይ የበኩላችሁን እንድትወጡ አርበኝነትን በመላበስ የራስን የአካባቢን ብሎም የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅና በፈቃደኝነት ወደ እዚህ አደረጃጀት በመምጣታችሁ በራሴና በከተማው አስተዳደር ስም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ በማለት በሚኖራችሁ ቆይታ በዝግጁነት በትጋት ህዝቡን ለማገልገል ብቁ በመሆን የተሻለ ስራ እንድትሰሩ አደራ እላለሁ ሲሉ ተደምጠዋል።

አቶ ታረቀኝ ወርቅነህ  የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ በበኩላቸው ህዝቡ ለከተማው ሰላም ዝግጁ ሆኖ ተጨማሪ ክህሎት ለማግኘት የሰላም ጉዳይ የኔ  ነው በማለት የህይወት እንዱ ክፍልና መሰረታዊና አስፈላጊ ወደ ሆነው ወደ ሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ለመቀላቀል በራስ ተነሳሽነት ስለመጣችሁ ምስጋና ይገባችሏል በማለት 

የሰላም ዋጋው ሰላም መሆን ብቻ ሳይሆን ወንጀሎች እየቀነሱ የመጡበት በርካታ ለውጦችም የታዩበት በአደረጃጀቱ ተሳትፎ ውስጥ ሆናችሁ ያለ ገደብ በምትፈለጉበት ጊዜአት ሁሉ  ተሳትፎአችሁ ከፍ እንዲል በማለት ሀገርንና  ቤተሰብን የሚያሳድግ የሚጠቅም ዕድልን በመጠቀም ከተማዋ የወንጀል መናኸሪያ ሳትሆን  ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚሄድበት የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በአደራ ጭምር አሳስበዋል ።

ስልጠናው በሁሉም ክ/ከተሞች ለተከታታይ አስር ቀናት በንድፈ ሀሳብና  በወታደራዊ መስክ ቀጥሎ እንደሚውል ተመላክቷል ።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79