7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲያ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲያልፍ የፀጥታ መዋቅሩ መውሰድ ባለበት ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ

7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲያልፍ የፀጥታ መዋቅሩ  መውሰድ ባለበት ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

ሚያዚያ 25/2018 ዓ.ም
(የአ.አ.ከ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከክ/ከተማ እስከ ወረዳ ለሚገኙ የዘርፉ አመራሮች ፣  ከየክ/ከተማው ለተውጣጡ መደበኛ የፖሊስ አካላት በ2018 ዓ.ም በሚካሄደው 7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሚያስችል ዕቅድ ላይ ውይይት ያካሄደ ሲሆን በመድረኩም የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ፣ የአ/አ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራን ጨምሮ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት  በ2018 ዓ.ም የሚካሄደው  7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ  የኢትዮጲያን መፃኢ ዕድል የሚወስንና ህዝቡም ዲሞክራሲን በመለማመድ ይሆነኛል የሚለውን መንግስት የሚመርጥበት እንደመሆኑ ፍፁም ሰላማዊና ፍትሀዊ መሆን እንዳለበት ገልፀው ለዚህ መሳካት የሰላምና ፀጥታ መዋቅሩ በስሩ የሚገኙ አደረጃጀቶችን በመጠርነፍ ከፖሊስ አካላት ጋር በመሆን በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል።

 አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ  የ2018 ዓ.ም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ለማድረግ የማስፈጸሚያ እቅድ ሲያቀርቡ እንዳሉት ሀገራዊ ምርጫው ሰላማዊ ፣ ዲሞክራሲያዊና ህብረተሰቡ መብቱን በአግባቡ መጠቀም እንዲችል የከተማዋን ሰላም ማስጠበቅና የፀጥታ ሀይሉ በየብሎክ ከተደራጁ የሰላም ሰራዊቶች ጋር በቅንጅት መስራት እንዳለበት ገልፀዋል።
 
በቀረበው ዕቅድ ላይ ሰፊ ውይይት ተካሄዶ የጋራ መግባባት ያዘዋል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79