ቢሮው ዘመኑን የዋጀ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ብቁ አገልግሎት የሚሰጥና የከተማውን ሰላምና ደህንነት የሚያረጋግጥ ባለሙያ በማፍራት ላይ ይገኛል ።
ቢሮው ዘመኑን የዋጀ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ብቁ አገልግሎት የሚሰጥና የከተማውን ሰላምና ደህንነት የሚያረጋግጥ ባለሙያ በማፍራት ላይ ይገኛል ።
አቶ ብርሀኑ ረታ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ሀላፊ
ሚያዚያ 24/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከማእከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ ለአራቱም ዘርፎችና ደጋፊ የስራ ሂደቶች ፣ ቡ/መሪዎችና ፈፃሚዎች በሁለተኛ ዙር በአካል ብቃትና በንድፈ ሀሳብ ዙሪያ ሰንዳፋ በሚገኝው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ።
ለሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በስነ ምግባር፣ በሀገር ወዳድነት ፣ የከተማ ደህንነት አጠባበቅ እና ወንጀል መከላከል ፣ በምርጫ ወቅት የፖሊስና የጸጥታ አካላት ሚና ፣ የመረጃ አሰባሰብና አያያዝ እና አጠቃቀም፣የማህበረሰብ ተሳትፊና ቅስቀሳ ፣ የህዝብ አገልግሎት አሰጣጥና የደንበኛ አያያዝ፣የዕቅድ አዘገጃጀት ላይ ብቃት ባላቸው አሰልጣኖች ሲሰጥ ቆይቷል።
ኮሚሽነር ተሻለ ሚቆሬ የኢትዮጲያ ፖሊስ ዮኒቨርስቲ የምርምር ማዕከል ፕሬዝዳንት በምረቃው ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲ በሀገር ደረጃ በከፍተኛ ደረጃ የምርምርና የስልጠና ተቋም መሆኑን አስታውሰው ቢሮው በሙሉ ልቡ ዩኒቨርስቲውን አምኖ ሀላፊነትን ስለሰጣቸው አመስግነው ሰልጣኞች ያገኛችሁት ዕውቀት ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ ስራ በመስራትና መጭው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ፍትሀዊ እንዲሆን የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድትወጡ አደራ እላለው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
አቶ ብርሀኑ ረታ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊና የሀይማኖት እና ሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ሀላፊ በበኩላቸው ቢሮው የሰራተኛው አቋም ለመገንባት ሲያስብ ቀዳሚ ምርጫው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ በማድረግ በሁለት ዙር ስልጠናው መሰጠቱን አንስተው ዩኒቨርስቲው ላደረገላቸው ትብብርና ድጋፍ አመስግነው ተቋሙ በከተማው አስተዳደር ደረጃ በየአመቱ በሚሰራው ስራ ተሸላሚ መሆኑን ጭምር ገልጸው ለዚህም ውጤት መመዝገብ የአመራሩና የሰራተኛ ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ገልጸዋል።
ም/ቢሮ ሀላፊው አያይዘውም ተቋሙ አቅሙን ይዞ እንዲቀጥል ከወቅቱ ጋር የሚሄድ ዘመኑን የሚዋጅ በትውልድ ቅብብሎሽ የሚሻገር ሀገሩን የሚያከብርና የሚወድ ብቁ አመራርና ሰራተኛ ለማድረግ እየተጋ ይገኛል በማለት አላማውን ማሳካትና ተወዳዳሪ ሆኖ መገኝት፣ ከዩኒቨርስቲው በስልጠና ያገኛችሁትን ዕውቀት ከትናንት በበለጠ የላቀ ተግባር ላይ በማዋል ለውጥ በማምጣት ይጠበቃል ብለዋል ።
አካልና አዕምሮን በማሰራት ልብን በመልካም ነገር በማዋል ለሌሎች መኖርን በመረዳት ለተሻለ ነገር መትጋት እንደሚያስፈልግ በማስገንዘብ የቢሮውን ተልዕኮ በማሳካት የተሻለ ነገርን በማዳበር በከተማው ላይ አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት ከተማ ማድረግ ይገባል ሲሉ ኃላፊው ተደምጠዋል ።
አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ በኩላቸውን ቢሮው በከተማው ላይ በርካታ ስራዎችን እንደሚያከናውን አስታውሰው የህግ የበላይነት የማረጋገጥ ስራውን በላቀ ውጤት ለማከናወን ከከፍተኛ አመራሩ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ ባለው ተዋረድ መሰረት በአመለካከትና በክህሎት የዳበረ በማድረግ በሁለት ዙር መሰጠቱ ተቋሙን የሚመጥን ኮርሶችን በመለየት እንደተሰጠና ከስልጠናው የተገኝውን ዕውቀት በሚገባ ተግባራዊ በማድረግ ህብረተሰቡን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል እንደሚገባቸውና ሀላፊነታቸውንም ጭምር እንዲወጡ አሳስበዋል።
በመጨረሻም ለሀገር ውለታ በመዋል ጉዳት ለደረሰባቸው የኢትዮጵያ ፊደራል ፖሊስ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች 132.300(አንድ መቶ ሰላሳ ሁለት ሺህ ሶስት መቶ ብር)በስጦታ መልክ ተበርክቶላቸዋል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79