7106 ህገወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ የንግድ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

7106 ህገወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ የንግድ ስርአት ማስገባት ተችሏል።

7106  ህገወጥ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ የንግድ ስርአት ማስገባት ተችሏል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ

       ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
        (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ የህግ የበላይነትና ቁጥጥር ግብረሀይል የአምስት ወር ከሁለት ሳምንት ያለውን የስራ አፈፃፀም   የግምገማ መድረክ  ያካሄደ ሲሆን በመድረኩም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላይ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ ፣ ክብርት ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ ፣ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራ አስኪያጅ  እንዲሁም የግብረሀይሉ አባላት ተገኝተዋል።

ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ  የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጠቅላይ አዛዥ  እንዳሉት   በግብረሀይሉ የተሰሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን አንስተው በሪፖርቱ ላይ ጥንካሬዎች እንዳሉ ሁነው የታዩ ክፍተቶችን ፈጥኖ በማረም ማስተካከል ያስፈልጋል ብለው በተለይም ከነዳጅ አቅርቦት ጋር በተያያዘ  በከተማዋ የሚታዩ እረጃጅም ሰልፎች እንዳይኖሩና ህጋዊ ስርአትን ተጠብቆ እንዲስተናግዱ ግብረሀይሉ  ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበትና በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የግብረሀይሉ ሰብሰቢ  እንደገለፁት ግብረ ሀይሉ በዋናነት የከተማዋ ያለውን የግብይት ስርአት ህጋዊ አድርጎ እንዲሄድ ማስቻል  መሆኑን ጠቁመው  ከተማው ውስጥ የሚገኝ ማንኛውም ነጋዴ ህጋዊነትን ጠብቀው እንዲሄዱ የማድረግ ፣  ንግድ ፈቃድ ሳይዙ የሚነግዱ ነጋዴዎችን ወደ ህጋዊ መንገድ የማስገባት ፣ አንዳንድ  ሰግብግብ ነጋዴዎች መጋዝን ውስጥ የሚያካማቹ  አካላትን ቁጥጥር በማድረግ ህብረተሰቡ ተገቢውን የግብይት ስርአት እንዲያገኝ ማስጠበቅ መሆኑን ገልፀው በዚህም በአምስት ወራት ውስጥ በግብረ ሀይሉ  ውጤታማ ስራ መስራት መቻሉን አብራርተዋል።

ኃላፊዋ አክለውም የነበሩ ጥቃቅን የሚመስሉ ክፍተቶች ላይ ግብረሀይሉ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባና በጥብቅ ዲሲፕሊንና በቅንጅት መስራትና ማስተካከል እንደሚገባ ገልፀዋል።

ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ  በበኩላቸው ግብረሀይሉ በተለይም ከንግድ ጋር በተያያዘ ህገወጥ ነጋዴዎችን ቁጥጥር የማድረግና ወደ ህጋዊ መንገድ ማስገባት ፣ ከነዳጅ ከቅርቦት አኳያ እንዲሁም አጠቃላይ መሰረታዊ ፍጆታዎች በተለይ ከበአላት መምጣት ጋር በተያያዘ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ግብረሀይሉ በትኩረት በመስራቱ ተጨባጭ ውጤት ማምጣት ተችሏል ብለዋል።

አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ የግብረሀይሉን የአምስት ወር ከሁለት ሳምንት የአፈፃፀም ሪፖርቱን በዝርዝር አቅርበዋል።

በውይይቱ ወቅት በግብረ ሀይሉ በከተማዋ የሚከናወኑ የንግድ እንቅስቃሴዎችን ፣ የሰላምና ፀጥታ ሁኔታን ፣ የንግድና የግብይት ሂደት ፣  ከወቅታዊ  የነዳጅ አቅርቦት ጋር በተያያዘ  እንዲሁም የደንብ ማስከበር ሂደት ላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራ በቅንጅት የተሰራበት አግባብ እንደነበርና  በዚህም ውጤታማ ስራዎች የተመዘገቡ  መሆናቸውን  ከተሳታፊዎች  ተነስቷል።

የተናበበና የተቀናጀ ወጥነት ያለው በእዝ የሚመራ ስምሪት ውስጥ መግባት ፣ ከአሰራር ውጭ የሚሄዱ ነጋዴዎች ላይ ጥብቅ ክትትል በማድረግ ወደ ህጋዊ ስርአት እንዲሄዱ ማስቻል፣ በሚሰጣቸው ማስተካከያ የማይሰሩና ወደ ህጋዊ ስርአት ያልገቡትን አስተማሪ እርምጃ መውሰድ ፣ ያለደረሰኝ ግብይት የሚፈፅሙትን እርማት እንዲወስዱ ማድረግ ፣ የብሎኪንግ ስራዎችን  አጠናክሮ ማስቀጠል ፣ የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረትን የመቆጣጠር ማጠናከርና የቅዳሜና ዕሁድ ገበያ ቦታዎች በቂ አቅርቦት እንዲይዙና ከደላላ ነፃ እንዲሆን የቁጥጥር ስራ መስራት ፣ በመንግስት ድጎማ የሚቀርቡ ግብአቶች በህብረት ስራ ማህበራት እንዲቀርቡ ማድረግ እንዲሁም የመጋዘን ፍተሻ ስራ ከአጎራባች ክ/ከተሞች ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚገባ የግብረሀይሉ ሰብሳቢ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የቀጣይ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79