የሰላም ሰራዊት አባላትን በማደራጀትና ብቁ የፀጥ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የሰላም ሰራዊት አባላትን በማደራጀትና ብቁ የፀጥታ አጋዥ ሀይል በማድረግ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የሰላም ሰራዊት አባላትን በማደራጀትና ብቁ የፀጥታ አጋዥ ሀይል በማድረግ  የከተማዋን ሰላምና ደህንነት የማስጠበቅ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

        ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም
        (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ከማህበረሰቡ የተመለመሉ የ7ኛ ኮርስ የሰላም ሰራዊት አባላትን አሰልጥኖ ብቁ የፀጥታ አጋዥ ሀይል ለማድረግ  ዝግጅት አድርጓል። 

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር  ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት ከተማችን አዲስ አበባ በፈጣን የልማትና የዕድገት ግስጋሴ ላይ እንደመሆኗ ሰላሟ የተረጋገጠባት እንግዶቿ ያለምንም የፀጥታ ስጋት የሚንቀሳቀሱባት ማድረግ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር ነው። ይህን ውጤታማ ለማድረግ የሰላም ባለቤት ህዝብ እንደመሆኑ ከነዋሪው  የተውጣጡ አዲስ የሰላም ሰራዊት ምልምሎችን በአካል ፣ በስነልቦና በፀጥታ አሰራርና ሰላም ማስጠበቅ ንድፍ ሀሳብ ዙሪያ በማሰልጠን ወደ ስራ ለማስገባት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልፀው ስልጠናውን ለሚሰጡ የፖሊስ ኦፌሰሮች አቅጣጫ ሰጥተዋል።

አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የስልጠናውን ይዘት  ስልጠናው ለሚሰጡ የፖሊስ አባላትና አስተባባሪዎች በንድፈ ሐሳብ፣ በማንቂያ ስፖርት እና በመስክ ወታደራዊ ዙሪያ ገለጻ ተሰጥተዋል።

ኃላፊው አክለውም  ማህበረሰቡ የአከባቢውንና የከተማዋን ሰላም በተጠናከረ  መልኩ ማስቀጠል እንዳለበት ገልጸው፤ ሰልጣኞችም ስልጠናውን በትኩረት ተከታትለው እንዲያጠናቀቁ አሳስበዋል።

በመጨረሻም  አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ምክትልና የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ  የ2018 ዓ.ም 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ለማድረግ የማስፈጸሚያ እቅድ አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።

https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79