የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በጋራ በመሆን የ2018 በጀት አመት የ9 ወራት እቅድ አፈጻጸም የሪፖርት ግምገማ መድረክ እያካሄዱ ይገኛሉ።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የሰላምና ፀጥታ ስራዎች በትኩረት መሰራት በመቻላችን በከተማችን  47 በመቶው የወንጀልና ወንጀል ነክ ጉዳዮች መቀነስ ተችሏል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ 
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ

ሚያዚያ 22/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮና ተጠሪ ተቋሙ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በጋራ በመሆን ከማእከል እስከ ወረዳ ካሉ የተቋማቱ የስራ ኃላፊዎች ፣  የክፍለ ከተማና የወረዳ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ዳይሬክቶሬቶች በተገኙበት  የ2018 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ገምግመዋል።

ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ  እንደተናገሩት  ከተማዋ ትልልቅ ሀገር አቀፍና አህጉር አቀፍ ሁነቶች የሚካሄዱባት የስበት ማእከል መሆኗን አዉስተዉ አዲስ አበባ በልማት እድገቷና ፍጥነቷ ልክ ዘላቂ የሆነ ሰላምና ደህንነት እንዲሰፍን ህዝቡን የሰላም ባለቤት አድርገን በመስራታችን በመጨመር እንጂ በመቀነስ የማናስተዉለዉ ስኬት በመደበኛ የወንጀል መከላከል እና በትላልቅ ሁነቶች ማየት ተችሏል ነዉ ያሉት።

ሀላፊዋ አያይዘውም ጨለማን ተገን ተደርገዉ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመቀነስ መንደሮችን በሙሉ በሚቻል መልኩ በብርሃን እንዲሞሉ፣ከወንጀል የጸዱ ብሎኮች እንዲኖሩ ህዝቡን የሰላም ባለቤት ካደረግንባቸዉ አደረጃጀቶች በሰላም ሰራዊቱ አማካኝነት በርካታ ስራ ተሰርቷል ያሉ ሲሆን፤በበጀት አመቱ የሁለቱንም ተቋማት የጸጥታ ተግባራት የቅንጅት ስራና የተቋም ግንባታ በዝርዝር አዉስተዉ፤ቢሮዉ ከአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ጋር በቅንጅት ያስጀመረዉ የአዉደ ሰላም የቴሌቪዥን ቶክሾ መርሃግብር ለሰላም ግንባታ ጅማሮ በመሆኑ በተለመደው ልክ ሰፊዉን ህዝባችንን ባሳተፈ መልኩ መጪዉ የምርጫ ጊዜ ያለምንም የጸጥታ ስጋት ዲሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ተቋማቱ ከመላው የጸጥታ መዋቅር በጋራ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል።

 የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ስራአስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ እንደገለፁት ሁለቱ ተቋማት በቅንጅት ህብረተሰቡን በማሳተፍ በከተማዉ  አስተማማኝ ጸጥታ እንዲሰፍን ባለፉት 9 ወራት በርካታ ስራዎችን፣የአደባባይ ኩነቶችንና የህዝብ በዓላትን በሰላም ተከብረዉ እንዲያልፉ መሠራቱን ጠቁመዉ፤ባሁኑ ወቅት ወደ ምርጫ ስራ በማተኮር የሚጠበቀዉን ተግባር እያከናወንን እንገኛለንም ብለዋል።

ስራ አስኪጁ አክለዉም በ9 ወር ዉስጥ በከተማዉ የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ ከማድረግ አንጻር የተሠሩ ስራዎችን በመገምገም በተያዘዉ 4ኛዉ ሩብ አመት የ2018 ዓ.ም ሰባተኛዉ ሀገራዊ ምርጫ በሠላም ተጀምሮ እስኪከናወን ድረስ ሁለቱም ተቋማት የሚጠበቅባቸዉን የጸጥታ ስራ ለመስራትና አንዱ ተቋም ከአንዱ ተቋም በመማር ጥንካሬን በማስቀጠል ክፍተቶችን እያረምን እንድንሄድ የሚያግዝ መድረክ ነዉ ሲሉም ተደምጠዋል።

በመድረኩ የሁለቱም ተቋማት የ9ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቦ ጥልቅ ግምገማ የተካሄደ ሲሆን፤በሪፖርቶቹም በበጀት ዓመቱ የጸጥታ መዋቅሩ በጥምር ሀይል በመገምገምና ጥብቅ ስምሪት በመስጠት እንዲሁም ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ የወንጀል ምጣኔ እንዲቀንስ የተሠሩ ስራዎች ፣ በከተማዉ የተካሄዱ አለም አቀፍና አህጉራዊ ኮንፈረንሶች ያለምንም የጸጥታ ስጋት  ዓላማቸዉ ላይ ብቻ  ትኩረት ተደርጎ መሠራቱ ፣ በመዲናዋ የተካሄዱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ህዝቡ የሰላም ባለቤት በማድረግ በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ በ9*ወራት ዉስጥ የተሠሩ ስራዎች ሲሆኑ፣ ህገ ወጥ የጎዳና ንግዶችን ለማስቀረት የተሰሩ ስራዎች ፣ አዋኪ ድርጊቶች ላይ እርምጃ የመውሰድ ተግባር ፣ ወንጀል ጠል የሆነ ማህበረሰብ እንዲኖሩ የተሰሩ ስራዎች፣ የኮሪደር ልማት ላይ የሚደርሱ ብልሽቶችን መቆጣጠርና  መሠል በከተማዉ ሰላምን አስፍኖ የህግ የበላይነትን ሊያረጋግጡ የሚያስችሉ አብይና አበይት ተግባራት በተቋማቱ ሪፖርት ላይ በስፋት ተነስቶ በበጀት አመቱ 47.5 ፐርሰንት የወንጀል ምጣኔ መድረስ መቻሉም ተገልጿል።

የተቋምን የመፈፀምና የማስፈፀም አቅምን ማጠናከር ፣ አሰራሮችን በማዘመን ማነቆ የሆኑ ጉዳዮችን ማስወገድ ፣ በሁለቱም ተቋማት የለሙ ቴክኖሎጂዎችን በተቋሙ ባለሙያዎች ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ፣  የሰላም ሰራዊቱን በስምሪትና በጥብቅ ድስፕሊን ብቁ በማድረግ ለመደበኛ የፀጥታ ሀይል አቅም እንዲሆኑ ማስቻል  ፣ የወንጀል መከላከል ስራዎቻችንን ማጠናከር ፣ የ7ተኛው ሀገራዊ  ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ እንዲሆን በትኩረት መስራት ፣ የመረጃ ትንተና ስራዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የሁኔታ አዝማሚያ ላይ ተጨባጭ ስራ መስራት ፣ የኢኮኖሚ አሻጥር ላይ የሚስተዋሉ ጉዳዮች ላይ ፣ የታክሲ ተርሚናሎች ዙሪያ ተገቢ ቁጥጥር መስራት ፣ የጫኝና አውራጅ ላይ እንዲሁም ቅንጅታዊ ስራዎች ላይ በትኩረት መስራት እንደሚገባ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።

በግምገማ መድረኩ  ላይ የሁለቱም ተቋማት የቢሮ ሀላፊዎች፣ምክትል የቢሮ ሀላፊዎች፣የክፍለ ከተማና የወረዳ የሰላምና ጸጥታ እንዲሁም ደንብ ማስከበስ ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣የማእከል ዳይሬክተሮች፣አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ጨምሮ ተሳትፈዋል።