የተሰሩ ስራዎች መገምገምና ክፍተቶችን ማረም ለተቋም ውጤታማነት ጉልህ ሚና አለው።
የተሰሩ ስራዎች መገምገምና ክፍተቶችን ማረም ለተቋም ውጤታማነት ጉልህ ሚና አለው።
ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም
(አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት በዕቅድ ይዞ ወደ ተግባር ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ስራዎችን በውጤታማነት እያከናወነ መሆኑ ተገለፀ።
በዛሬው ዕለት የቢሮው የትግበራ ክንውን በሰነድ በተደገፈ መልኩ ከአዲስ አበባ ፕላን ኮምሽን የተወጣጡ አካላት በተደረገ ግምገማ ሂደቱን በዝርዝር ማሳየት ተችሏል።
ቢሮው በአራት ዋና ዋና ዘርፎች ተደራጅቶ የሚሰራ ሲሆን፡-
1. የኃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ
በዚህ ዘርፍ የኃይማኖት ተቋማትን መገንባት፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም ማህበረሰቡ የሰላም እሴቶችንና አብሮነትን እንዲጠናከር በየብሎኩ የ“ቡና ጠጡ” ፕሮግራሞች በማካሄድ በአከባቢ ሽማግሌዎች እና ወላጆች የሚመራ የማስታረቅ ስራ እንዲሁም የበጎ ፈቃድ ወጣቶችን በመለዋወጥ ከክልሎች መካከል ባህልና ዕሴት ልውውጥ ማበረታታት ተከናውኗል።
2. የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ
የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ የተለያዩ ማህበራዊ አደረጃጀቶች ተመስርተው በተለይም የ“ሰላም ሰራዊት” አባላትን ፣ የጫኝና አውራጅ ማህበራትን የማደራጀት የመደገፍ ፣ የፓርክንግ አገልግሎት የሚሰጡ ወጣቶችን ወደ ስራ በማስገባት ሰላሟ የተረጋገጠባት ከተማን በማረጋገጥ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ ተችሏል።
3. የፀጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ
በከተማዋ የሚፈጠሩ ወንጀሎችን በቅርብ በመከታተል በርካታ ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ ኦፕሬሽን የተካሄደ ሲሆን፣በዚህም ፔንስዮኖች፣ ቤቲንግ ቤቶች እና ማሳጅ ቤቶች የማሸግ እርምጃ የመውሰድ ፣ አካባቢዎችን በመብራት የተሞሉ ማድረግና የደህንነት የሲሲቲቪ ካሜራ በመግጠም ወንጀልን በከፍተኛ ሁኔታ መቀነስ መቻሉን ተገልጿል።
4. የፀጥታና መረጃ ዘርፍ
በአደባባይና በሆቴሎች የሚካሄዱ ፕሮግራሞችን ፍቃድ መስጠት፣ የወንጀል አዝማሚያዎችን መከታተል፣ መቆጣጠር እና ተገቢ እርምጃ የማስወሰድ ስራ ተከናውኗል።
በአጠቃላይ ቢሮው በተከናወኑ ስራዎች ግምገማዎች በማድረግ የተገኙ ውጤቶችን ማጠናከርና ያሉ ክፍተቶችን በመለየት ማረም በተቋሙ ውጤታማነት ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እያደረገ መሆኑ ተጠቅሷል።