ለተቋሙ ሰራተኞች በሰንዳፋ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ የሚገኝው ስልጠና ቀጥሏል።
ለተቋሙ ሰራተኞች በሰንዳፋ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ የሚገኝው ስልጠና ቀጥሏል።
ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር ከማእከል እስከ ወረዳ ለሚገኙ የስራ ሂደቶች ፣ ቡ/መሪዎችና ፈፃሚዎች በሁለተኛ ዙር በአካል ብቃትና በንድፈ ሀሳብ ሰልጣኞች ሰንዳፋ በሚገኝው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል ።
ለሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች በስነ ምግባር፣በሀገር ወዳድነት፣በወንጀልና ደህንነት አንዲሁም የከተማ ደህንነት እና ወንጀል መከላከል ላይ ብቃት ባላቸው አሰልጣኞች እየተካሄደ ይገኛል።
የስልጠናው ዓላማ ሰራተኞች የተቋሙን የመፈጸምና የማስፈጸም ሁኔታ ይበልጥ በማስቀጠል በአካልና በአዕምሮ በማጎልበት የተሻለ ዕውቀትን አፍርቶ ሀገርን በታማኝነት ህብረተሰቡን በቅንተን በማገልገል የአዲስ አበባን ከተማ ሰላም ይበልጥ አጠናክሮ ማስቀጠል ነው።
አቶ ጌታሁን አበራ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ አማካሪ እስካሁን ያለውን የስልጠና ሂደትና ሌሎችም በተመለከተ በቦታው በመገኝት ባደረጉት ምልከታ እጅግ ደስ የሚል ከቀን ቀን በጥልቅ ስነ ስርዓት እየተመራ የሚገኝ ተደማሪ አቅም እየፈጠረ የሚገኝና ነው በማለት ከስልጠናው በኋላም ወደ ተቋም በምንመለስበት ወቅት ሀገርን በማጽናት በመከባበር በመቻቻል አንድነትን ከጉልቶ በማውጣት የተቋምን ግንባታ ክህሎት ዕውቀት በማሻሻል ለተሻለ ስራ መትጋት እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
አማካሪው አያይዘውም በሚቀሩት ቀሪ ቀናት የስልጠናውን መርሐ ግብር አጠናክሮ በማስቀጠል አሁን ባለው ልክ በጥሩ ስነ ምግባር በመቀጠል ያሉ ክፍተቶችም ካሉ በመነጋገር ስልጠናው በተፈለገለት ልክ እንደሚቀጥል ማድረግ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79