የተቋምን ተልዕኮ በላቀ ውጤት ለማጠናቀቅ ብቁ አመራርና ሰራተኛ መኖር ወሳኝ ነው።
የተቋምን ተልዕኮ በላቀ ውጤት ለማጠናቀቅ ብቁ አመራርና ሰራተኛ መኖር ወሳኝ ነው።
ሚያዚያ 15/2018 ዓ.ም
(አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ )
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከኢትዮጲያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ከማእከል እስከ ታችኛው መዋቅር ለሚገኙ የዘርፉ አመራሮች ፣ ዳይሬክቶሬቶች ፣ ቡ/መሪዎችና ፈፃሚዎች በፀጥታ አመራርነትና በሁለንተናዊ ንድፈ ሀሳብ ዙሪያ እየሰጠ ያለውን ስልጠና ቀጥሏል።
በስልጠናው ሂደትም በከተማ ደህንነት አጠባበቅ ፣ በወንጀል ምንነትና መከላከል እንዲሁም በፀጥታ ማስጠበቅ ዕቅድ አዘገጃጀት ላይ በብቁ የዩኒቨርስቲው መምህራን በጥልቀት እየተሰጠ ሲሆን ሰራተኛው በአካል የዳበረ በአይምሮው የበለፀገ እንዲሆን የሚያስችሉ የአካል ብቃት ስልጠናዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ።
አቶ ፍስሀ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ም/ቢሮ ኃላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ በስልጠናው መሀል የከተማዋን ሰላም ከማረጋገጥ አኳያ በቀጣይ የፀጥታ አመራሩ ከህዝብ አደረጃጀትና የሰላም ባለቤት ህዝብን ከማድረግ አንፃር የሚሰሩ ስራዎችን ግንዛቤ ሲስጡ እንዳሉት የነባር የሰላም ሰራዊት አባላት የስራ አቅጣጫ መስጠትና 165 ሺህ በላይ ነባር የሰላም ሰራዊት አባሉንና የቅጥር ጥበቃን ማስቀጠል እንዲሁም አዲስ የሰላም ሰራዊት አባላት የምልመላ ሂደትና ማሟላት ስለሚገባቸው ጉዳዮች በዝርዝር አሰገንዝበዋል።
በዩንቨርስቲው ከዕለታዊ የአካል ብቃት ልምምድ ባሻገር የእግር ኳስ ጨዋታም በመአከልና በክ/ከተማዎች መካከል ተካሂዷል።
የአጠቃላይ የስልጠና ሂደቱም አመራሩንና ሰራተኛውን በአካል የዳበረ በአምሮ የበለፀገና ከዘመኑ ጋር የተወዳጀ እንዲሆንና አዲስ አበባ ከተማ ሰላሟ የተረጋገጠ ህዝቦቿ የለምንም የፀጥታ ስጋት መንቀሳቀስ እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑ ተመላክቷል።
https://linktr.ee/qr/e5702bda-a953-4926-8253-c3bd2f978c79