የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ እና የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽን ቢሮ በጋራ ያበለጸጉትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተመለከተ ከአስራአንድም ክፍለ ከተሞች የተመረጡ ወረዳዎች ለአስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ማብራሪያ ተሰጠ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ እና የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽን ቢሮ በጋራ ያበለጸጉትን ዘመናዊ ቴክኖሎጂ በተመለከተ ከአስራአንድም ክፍለ ከተሞች የተመረጡ ወረዳዎች ለአስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች ማብራሪያ ተሰጠ።
የካቲት 24/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.ቢ)
በመድረኩ ላይ የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ እንደገለጹት፣ ቢሮው ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የሃይማኖት እምነት ተቋማት ጋር የመረጃ ልውውጥን ማዘመን አስፈላጊ መሆኑንና በተለይም መረጃ ማደራጀት፣ ድጋፍና ክትትልን በኦንላይን ስርዓት ማከናወን፣ ዕለታዊ መረጃዎች፣ ዕቅድና ሪፖርቶችን በተደራጀ መልኩ መላክ የሚያስችልና ቴክኖሎጂው ጊዜ ቆጣቢ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የስራ ሂደት እንዲፈጠር የሚያግዝ መሆኑን አብራርተዋል።
በበለጸገው ቴክኖሎጂ ላይ ማብራሪያ የሰጡት የኢኖቬዥን ቢሮ ቴክኖሎጂ ባለሙያ አቶ ዳንኤል ርዕሶም ሲሆኑ፣በገለጻቸውም 1ኛ የሃይማኖት ተቋማት መረጃዎችን በስርዓቱ እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል፣2ኛ በተቋማቱ ላይ የሚቀርቡ ቅሬታዎችና አቤቱታዎችን በዲጅታል መንገድ መላክ፣መፍታትና መከታተል የሚቻልበትን ሂደት፣3ኛ የድጋፍና ክትትል ስርዓት እንዲሁም ዕቅድና ሪፖርት በተደራጀ መልኩ እንዴት መላክ እንደሚቻል በዝርዝር አብራርተዋል።
በውይይቱ ወቅት ከአስራንዱም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም ከተመረጡ ወረዳዎች የተሳተፉ አባላት ጥያቄና አስተያየት አንስተው፣መድረኩን የመሩት እና የዘርፉ ዳይሬክተሮች በቴክኒክና በአስተዳደር ደረጃ መስተካከል የሚጠይቁ ጉዳዮች ተለይተው እንደሚስተካከሉ እና ግብዓቶች ለመውሰድ እንደሆነም ገልጸዋል።
የቢሮው ዘርፍ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎች የአስራንዱም ክ/ከተሞች የዘርፉ አስተባባሪዎች እና የተመረጡ የወረዳ ቡድን መሪዎች ተገኝተዋል።