በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት ቀሪ የ6 ወራት የተከለሰ ዕቅድ ላይ የውይይት ተደረገ።

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት ቀሪ የ6 ወራት የተከለሰ ዕቅድ ላይ የውይይት ተደረገ።

  የካቲት 24/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
*****

ኢ/ር ፍቃዱ አቶምሳ በፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ የወንጀል መከላከል፣የፀጥታ ኦፕሬሽንና ግጭት አፈታት  ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የእንኳን ደህና መጣቹና የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣በንግግራቸውም ወቅት፣ ያለፉት 6ወራት አፈፃፀምን በመገምገም በቀሪው ጊዜ የሚከናወኑ የሰላምና ደህንነት የፀጥታ ተግባራትን ለማጠናከር ተደራሽና ውጤታማ ለማድረግ እንደሆነና  በተቀመጠው አቅጣጫና በታቀደው ዕቅድ መሰረት መሰራት እንዳለበትም ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም በውይይቱ ወቅት በቀሪው የበጀት ዓመት ጊዜ ውስጥ ዕቅዱን በትክክል በመፈፀም የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ በተጠናከረ ቁርጠኝነት እንዲሰራ እና ተግባራት ላይ ዋና ዋና ግቦች ምን ምን መሰራት አለበት የሚለውን በማየት፣በተለይም በቁጥር የሚለኩ ላይ ትኩረት እና ግቡን መነሻ በማድረግ መሰራት አንደሚገባም አሳስበዋል።

የተከለሰውን ዕቅድ ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ዳምጠው አያሌው የማህበረሰብ አቀፍ የፀጥታ አጠባበቅ እና የተቋማት ደህንነት ክትትል ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ፣በገለጻቸውም በተከለሰው የዕቅድ ውይይት ማድረግ ዋና ዓላማው የከተማዋን ፀጥታ ለማጠናከር፣ የወንጀል መከላከልን ለማበርታት፣ከማህበረሰቡ ጋር ያለውን ቅርብ ትብብር ለማሳደግ እና በዘርፉ ወጥ የሆነ ዕቅድና ሪፖርት ከማዕከል እስከ ወረዳ እንዲኖር፣አንድ ዕቅድ አንድ ሪፖርት መርሃ ግብርን ተግባራዊ ማድረግ እና በዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ያጋጠሙ ውስንነቶችን ማረም  እንዲሁም የተለያዩ  የዘርፉን ቁልፍ አመላካች ተግባራዊ ማድረግ እንደሆነ በሪፖርቱ አብራርተዋል።

39ኛው የአፍሪካ መሪዎች ጉባኤ እና 130ኛው የአድዋ ድል በዓልን ያለምንም ፀጥታ ችግር በሰላም እንዲያልፍ፣ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ የዘርፉ ሰራተኞች፣የፀጥታ አካላት እና የማህበረሰቡ አስተዋጽኦ እንደሆነ ጠቅሰው፣የዛሬው መድረክ ውይይት ዕቅድ ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነና ዕቅዱ መነሻና መዳረሻ የሌለው ዕቅድ እንዳይኖር ያለመ ውይይት እንደሆነና በተለይም ተቋሙን የሚገለጸው፣ሰዓትና ጊዜ የሚያመለክት ዕቅድ መሆን አለበት ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ም/ል ቢሮ ኃላፊና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድር ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም የታቀደው ዕቅድ መነሻ በማድረግ እና የክ/ከተማውን ነባራዊ ሁኔታ በማስፋት ማቀድ እንዳለባቸውና እንዲሁም ህብረተሰቡ ላይ ትኩረት በማድረግ የግጭት አፈታትንም ጭምር ዕቅድ ውስጥ በማስገባት ማቀድ እንደሚገባም አሳስበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች ባነሷቸው ጥያቄና አስተያየቶች ላይ ውይይት ተደርጎበታል። 

በውይይቱ መድረክ ላይ ከማዕከል እስከ ወረዳ የሚገኙ የዘርፉ ዳይሬክተሮች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።