በ8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በ8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ እየተሳተፉ የሚገኙ የክልል ም/ል ርዕሰ መስተዳደሮችና የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የሰላምና የፀጥታ ሥራዎችን ምልከታ አደረጉ፡፡

በ8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ  እየተሳተፉ የሚገኙ የክልል ም/ል ርዕሰ መስተዳደሮችና የሰላምና ፀጥታ ኃላፊዎች በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የሰላምና የፀጥታ ሥራዎችን ምልከታ አደረጉ፡፡

   የካቲት 21/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
      **

በቦሌ ክ/ከተማ እና በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የማህበረሰብ አቀፍ፣በየብሎኩ የሚከናወኑ የቡና ጠጡ የኮሚኒቲ ዲያሎግ ፕሮግራሞችን እና የተገጠሙ የሲሲቲቪ ካሜራ ስራዎችን ጎብኝተዋል።

8ኛው ሀገራዊ የሰላምና ጸጥታ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ንግግር ያደረጉ እና ጉብኝቱን የመሩት አቶ ፍሰሐ ጥበቡ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ም/ል ቢሮ ኃላፊ እንደተናገሩት በማህበረሰብ አቀፍ ተሳትፎና አደረጃጀቶችን በማደራጀት በከተማዋ የነበሩ የወንጀል ምጣኔን መቀነስ መቻሉን በማንሳት፣ክልሎችም ከዋናው ስራ አስፈጻሚ ጀምሮ እስከ ታች ወረዳ እና ህብረተሰቡ ውስጥ ወርዶ በቅንጅት በመስራትና የተሰሩ ስራዎችን በመገምገም ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል ገልጸዋል።

በከተማው ውስጥ በዶክመንተሪ ስናየው የነበረውን  በመዘዋወር በተለይም የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት በተግባር ማየታቸውን ገልጸው፣ከተማችን አዲስ አበባ ላይ ምንም ዓይነት ህገ ወጥ ተግባሮችን ወንጀሎችን እንዳይፈጠር እና ሰላማዊ እንድትሆን አድርጓል ሲሉ  አቶ መብራቱ ካሳ የሰላም ሚኒስቴር ጽ/ቤት ኃላፊ ገልጸዋል።

ኃላፊው አክለውም ይህም ለሀገራችን ትልቅ መሰረት የጣለ ሲሆን፣ክልሎችም የተጀመሩ ጉዳዮችን በማስፋት የክልሎችንና የአከባቢያቹን ሰላም ማረጋገጥ አለባቹ ሲሉ አሳስበዋል።

ከክልል የመጡ እንግዶችም፣በከተማዋ ያየነው የፀጥታና የልማት በተለይ የህብረተሰብ ተሳትፎ ላይ የተሰሩ ስራዎች ይበል የሚያስብል እና ማህበረሰቡ በራሱ ተሳትፎ ችግር ፈቺ በመሆን ዘላቂ ሰላምን ማምጣት መቻሉ ለኛ ለክልልሎች ትልቅ ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል።

የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አድማሱ ደቻሳ፣የእንኳን ደህና መጣቹ ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣በክ/ከተማችን የተለያዩ አደረጃጀቶችን በማደራጀትና ማህበረሰቡን የሰላም ዘብ በማድረግ ከፖሊስና ከፀጥታ አካሎች ጋር በማቀናጀት በ7/24ስምሪት ወስደው መስራታቸውን ገልጸው፣በተለይም ህዝብን ማዕከል በማድረግ፣የሰላም ጉዳይ ቅድምያ በመስጠት በመስራታችን ውጤት ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል።

በመጨረሻም በነበረው ቆይታ ላይ የዕውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም ተደርጓል።