8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በከተማው የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎችን ጎበኙ።
8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በከተማው የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎችን ጎበኙ።
የካቲት 20/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
******
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት ያስጀመረው 8ኛው ሀገራዊ የሰላምና ጸጥታ የምክክር መድረክ ተሳታፊዎች በከተማው የወንጀል ምጣኔን ለመቀነስ የተሰሩ ስራዎችን በቦሌ ክ/ከተማ በመገኘት ጉብኝት አድርገዋል።
በጉብኝቱ ወቅት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ቸሩ ጌታ ባደረጉት ንግግር የአዲስ አበባ ሰላም የተጠበቀ እንዲሆን የተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤት ማስመዝገባቸውን አውስተው፣ "ዛሬ በቦሌ ክፍለ ከተማ ያደረግነው ጉብኝት የከተማዋን ሰላም ለማስጠበቅ የሰላም ሠራዊት እና የጸጥታ መዋቅሩ ከብሎክ አንስቶ ያከናወነውን ተግባር በአካል በመመልከት ክልሎች ተመክሮ እንዲወስዱ የሚያስችል ነው" ብለዋል።
ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ከፍተኛ በሆነ የልማት አውድ ውስጥ በመሆን የሰላም ሰራዊት አባላትን ከፀጥታ አካላት ጋር በማስተሳሰርና በማቀናጀት በሶስት ሽፍት በማሰማራት መረጃን በመስጠትና የወንጀል ስጋትን በመከታተል የወንጀል ምጣኔን በከተማች ላይ መቀነስ መቻሉን ጠቅሰው፣ክልልሎች ይሄንን ልምድ በመውሰድ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ ሰላምን በዘላቂነት ማስጠበቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።
የቦሌ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኩራ እንደተናገሩት የከተማችንን ሰላም ለማስጠበቅ ህዝቡን የሰላም ባለቤት በማድረግ፣ከሰላም ሰራዊት አባላትና ከፀጥታ አካላት ጎን በመሆን በቅንጅትና በመተባባር ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አንስተዋል።