8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክ...

image description
image description
image description
image description
- recent news   

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ እስከ አሁንም ድረስ እየተካሄደ ይገኛል።

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

የሰላም ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ጋር በመተባበር 8ኛውን ሀገራዊ የሰላምና ጸጥታ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ መሀመድ እድሪስ በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን አንፃራዊ ሰላም ሰፍኗል ያሉ ሲሆን ለዚህ ውጤት መሳካትም የሕዝባችን የሰላም ፍላጎት፣ተግቶ የሚሰራ አመራር መኖር ፣የጸጥታ አካላት ጥምረት እና ለዘመናት የኖሩ ማኅበራዊ እሴቶቻችን ዋና ዋና ምክንያቶች ናቸው ብለዋል፡፡

መንግሥት ለሰላም ሁልጊዜም ቅድሚያ ይሰጣል ያሉት ክቡር ሚኒስትሩ በተሳሳተ መንገድ በመሄድ ትጥቅ ይዘው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ አካላት ጋር ውይይት በማድረግ የሰላም አማራጭ እንዲቀበሉ አድርጓል ብለዋል፡፡

አክለውም የመንግሥት ፍላጎት ሁልጊዜም ቢሆን ሰላም  መሆኑን ገልፀው ፤ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የሕዝባችን እና የጸጥታ አካላት ጥምረት ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል፡፡

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ  ዓላማ በወቅታዊ ሀገራዊ የሰላምና የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ውይይት እና የልምድ ልውውጥ በማድረግ በፌዴራል እና በክልል የሰላምና የጸጥታ ተቋማት መካከል ቅንጅትን፣ ተግባራዊ ትብብርን እና የጋራ መግባባትን ማጠናከር ነው፡፡፡

በመድረኩ ላይ የፌዴራል እና የክልል የሰላምና የጸጥታ ከፍተኛ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች  እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡