8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክ...

image description
image description
image description
image description
- recent news   

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

የካቲት 20/2018 ዓ.ም 

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከሰላም ሚኒስቴር  ጋር በመተባበር 8ኛውን ሀገራዊ የሰላምና ጸጥታ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ጊዜያት ትልልቅ ሀገራዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለማቀፋዊ ሁነቶች ተካሂደዋል ያሉ ሲሆን ይህም የሆነው በከተማዋ አስተማማኝ ሰላም ስለሰፈነ ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምን ለማስጠበቅ የፀጥታ አካላት ከሕዝባችን ጋር በመሆን ሌት ከቀን እየሰሩ ይገኛሉ ያሉት ክብርት ሊዲያ የተፈጠረው የሰላም ሠራዊት አደረጃጀት እና የማኅበረሰብ አቀፍ ውይይቶች ትልቅ ለውጥ አምጥተዋል ብለዋል፡፡

8ኛው ሀገር አቀፍ የሰላምና ጸጥታ የጋራ የምክክር መድረክ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንደቀጠለ ነው፡፡