በሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
በሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ የሚሰጡ አገልግሎቶችን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
የካቲት 17/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለሃይማኖትና ለሰላም ዕሴት ግንባታ ዘርፍ አገልግሎቶችን የተሻለ ለማድረግ የከተማው የኢኖቬዥን ቢሮ ያበለጸገው ቴክኖሎጂ በተመለከተ ለዘርፉ ዴይሬክተሮችና ለቡድን መሪዎች ማብራርያ ሰጥተዋል።
ማብራርያውን የሰጡት የኢኖቬዥን ቢሮ የቴክኖሎጂ ባለሙያ አቶ ዳንኤል ርዕሶም ሲሆኑ፤ በገለጻቸውም ወቅት 1ኛ/ነባርና አዲስ የሃይማኖት ተቋማትን እንዴት በስርዓቱ መመዝገብ እንደሚቻል
2ኛ/በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚስተዋሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን (ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን) በዲጅታል ስርዓት እንዴት እንደሚቀበሉ፣ እንደሚፈቱና እንደሚከታተሉ
3ኛ/የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤን በየደረጃው የድጋፍ እና ክትትል ስርዓትን በተደራጀ መንገድ እንዴት አድርገው ማድረግ እንዲችሉ ማብራሪያ ተሰጥተዋል።
በቀረቡት ነጥቦች ላይ ዳይሬክተሮችና ቡድን መሪዎቹ ጥያቄና አስተያየት አንስተው የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊና የዘርፉ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ መስተካከል የሚጠይቁ ጉዳዮች በቴክኒክና በአስተዳደር ደረጃ ተለይተው እንደሚስተካከሉ እና ወደፊት በሃይማኖት ተቋማት ላይ የሚተገበሩ አዳዲስ አዝማሚያዎችን ቴክኖሎጂው እንዴት እንደሚያካትት አስተያየት ሰጥተዋል።
አቶ ብርሃኑ አክለውም የለማውን ቴክኖሎጂ በሙከራ ደረጃ ለመተግበር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ እና ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ በሁለት ወረዳዎች ተመርጠው በ24/06/2018 ዓ.ም የሙከራ ሥራ እንዲጀምር ቀጠሮ መያዙን ገልጸዋል።
በሙከራው ውጤት መሰረትም ቴክኖሎጂው በሌሎች ክፍለ ከተሞች ደረጃ በስፋት እንደሚተገበር ጠቁመው፣
ቴክኖሎጂው በሃይማኖት ተቋማት ዘርፍ የመረጃ አስተዳደርን ለማዘመን፣ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማጠናከር እንዲሁም የሰላም ዕሴቶችን ለማጎልበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።