የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የለማ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችል ስልጠና፣ የግንዛቤ ማስጨበጫና ውይይት አካሄደ።
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት የለማ ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ ለመሆን የሚያስችል ስልጠና፣ የግንዛቤ ማስጨበጫና ውይይት አካሄደ።
የካቲት 13/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
*****
ስልጠናው ለየግል ጥበቃ ኤጀንሲዎች፣ ለመንግስትና ለግል ተቋማት እንዲሁም ለሞተር ማህበር ሰብሳቢዎች የተዘጋጀ ሲሆን በፀጥታ ስራዎች ውስጥ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የቅድመ መከላከልና የክትትል አቅምን ለማጠናከር ትኩረት ተሰጥቶበታል።
በዚህ ወቅት የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ደንድር እንደገለጹት፣ የከተማዋን ዘላቂ ደህንነትና ሰላም ለማረጋገጥ የተቋማት ደህንነት መረጃ መለዋወጫን ከዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎች ጋር በማቀናጀት መስራት አስፈላጊ መሆኑንና፣ይህም ወንጀል ከመፈጠሩ በፊት ለመከላከልና ከተከሰተ በኋላ በፍጥነት ቁጥጥር ለማድረግ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል።
እንዲሁም ሀላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅት የወንጀል አፈጻጸም እየራቀቀ መምጣቱን በመግለጽ፣ የተሰጠውን የቴክኖሎጂ ስልጠና በተግባር በማዋል የቅድመ መከላከልና የመቆጣጠር ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አሳስበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ የኤኖቬዥን ቢሮ የሶፍትዌር ባለሙያ አቶ ጌታቸው በሪሁን በለማ ቴክኖሎጂ ስልጠና ላይ ለተሳታፊዎች የፅንሰ-ሐሳብና የተግባር ስልጠና የሰጡ ሲሆን፣ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች በፀጥታ አገልግሎት ላይ ያላቸውን ሚና በማብራራት በፅንሰ-ሐሳብ ደረጃ ገለጻ እና
በተጨማሪም ሰልጣኞች ቴክኖሎጂውን በተግባር እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ በተሞክሮ የተደገፈ ስልጠና ሰጥተዋል።
ቢሮው በቀጣይም ከሁሉም የፀጥታ ተዋናዮች ጋር በቅንጅት በመስራት የከተማዋን ሰላምና ፀጥታ ለማጠናከር የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን እንደሚያስፋፋ እና የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትን በማሳደግ የቅድመ መከላከልና የክትትል ስራዎችን ለማጠናከር እንደሚያግዝ ገልጿል።
በስልጠናውም የቢሮው ም/ል ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንድርን ጨምሮ፣የኤጀንሲዎች ባለቤት፣በኤጀንሲ የሚጠበቁ የተቋማት ኃላፊዎች፣ስልጠናውን የሚወሰዱ የኤጀንሲና የተቋማት ባለሙያዎች እና የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉ ዳይሬክተሮች፣አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።