የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማዋን ወቅታዊ የፀጥታና የደህንነት ሁኔታ ገመገመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የከተማዋን ወቅታዊ የፀጥታና የደህንነት ሁኔታ ገመገመ፡፡

የካቲት 12/06/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ ፓሊስ ኮሚሽን ጠቅላይ መምሪያ አመራሮች፣ ከ11ዱም የክ/ከተማ የሰላምና ፀጥታ ፅ/ቤት ኃላፊዎች፣ ከፀጥታ መረጃና  ኦፕሬሽን ዳሬክተሮችና አስተባባሪዎች ጋር በጋራ በመሆን ወቅታዊ የከተማዋን የፀጥታ ሁኔታ ገምግሟል፡፡

መድረኩን የመሩት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ እንዳሉት ቢሮው የከተማዋን ሰላም አሰተማማኝና ዘላቂ ለማድረግ በርካታ የሰላምና ፀጥታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን በመግለፅ፤ ከነዚህም አንዱ እና ዋነኛው የከተማዋን ነዋሪ በማሳተፍ የከተማውን ሰላምና ጸጥታ አስተማማኝ በማድረግ ህዝቧ በሰላም ወጥቶ እንዲገባ ማድረግ አንዱና ዋነኛው እንደሆነና  ይህንንም ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ዘርፈ ብዙ ስራዎች እተከናወኑ እንደሚገኙ አንስተዋል፤

ክብርት የቢሮ ኃላፊዋ አክለውም ከተማዋን የጥፋት እና የሽብር ከተማ ለማድረግ ይህንን ዘላቂና አስተማማኝ ሰላም የማይፈልጉና የከተማውን ነዋሪ እንዲሁም ከተማዋ በአለምአቀፍ ሃገራት ያላትን ተመራጭነት ለማሳጣት በርካታ የሽብር ሀይሎች በውጪም በውስጥም የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ እንደሚገኙና ይህንን የሚመጥን የፀጥታ ስራ መሰራት እንዳለበት ገልፀዋል፤

በከተማው የሚስተዋሉ አዋኪ ተግባሮችና በየጊዜውና መልካቸውን በመቀያየር የሚፈፀሙ የረቀቁ ወንጀሎች ላይ የቅድመ ልየታ ስራዎችን በመስራት የማስተካከል ስራ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ወቅታዊ የከተማውን የፀጥታ ሁኔታ የሚያመላክት ሰነድ በኢ/ር ፍቃዱ አቶምሳ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ዳይሬክቶሬት ዳሬክተር ቀርቦ ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎበት መመሪያ ተሰጥቶበታል።

በመድረኩ ላይ ክብርት የቢሮ ኃላፊዋን ጨምሮ ኮሚሽነር ፍቅሩ አለማየሁ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጠቅላይ መምሪያ ም/ኮሚሽነር፤ አቶ ተስፋዬ ደንድር በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ም/ቢሮ ኃላፊ፤ የክ/ከተማ ፅ/ቤት ኃላፊዎ እና የፀጥታ ኦፕሬሽን ዘርፍ ስራ አስተባባሪዎች ተገኝተዋል፡፡