የትስስር ሰነድ የፊርማ ስነ-ስርአት ተካሄደ።

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

የትስስር ሰነድ የፊርማ ስነ-ስርአት ተካሄደ።

በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ መካከል በጋራ መስራት የሚያስችል የትስስር ሰነድ የፊርማ ስነ-ስርአት ተካሄደ።

     የካቲት 12/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
                       *****

የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ እና የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ስምምነት የፊርማ ስነ-ስርዓት አድርገዋል። 

የፊርማው ዓላማ በአዲስ አበባ ዘላቂና አስተማማኝ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ የሚዲያ ሚናን ማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።

የቢሮው ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት፣ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እና የተለያዩ አለም አቀፍ ጉባኤዎች የሚካሄዱባት ከተማ መሆኗን ጠቁመው፣በዚህ ምክንያት የከተማዋ ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ለሀገር ያለው አደምታ ከፍተኛ መሆኑን እና እንዲሁም የሰላምና ፀጥታ ጉዳይ የፀጥታ አካላት ብቻ ሀላፊነት ሳይሆን፣ ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት በማድረግና በንቃት በመሳተፋቸው፣እንደሆነ አመላክተው በዚህ ሂደት ሚዲያዎች ግልፅኝነትና ታዓማኒነት ያለው መረጃ በማቅረብ ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸዋል።

የአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ካሳሁን ጎንፋ እንዳሉት፣ አዲስ አበባ የኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች ማዕከል ስትሆን፣ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመዋል።

አቶ ካሳሁን አክለውም፣አዲስ ማዲያ ኔትወርክ ከመንግስትና ከህዝብ መካከል የመረጃ ድልድይ ሆኖ በሰላምና ፀጥታ ዙሪያ የሚከናወኑ ስራዎችን በማቀናጀት ለህብረተሰቡ ለማድረስ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸው፣የዛሬው ፊርማ መፈራረም ውጤቱን በቀጣይ በመገምገም እና በማጠናከር እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል።