የሲቪክና የሙያ ማህበራት በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።
የሲቪክና የሙያ ማህበራት በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ያላቸው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ።
የካቲት 09/2018 ዓ.ም (አ.አ.ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
*****
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ በ2018 በጀት ዓመት በከተማዋ የሚገኙ የሲቪክ፣ የብዝኃንና የሙያ ማህበራት ተወካዮችን ያካተተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አካሄደ።
በተካሄደው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ወቅት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል ቢሮ ኃላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍሰሐ ጥበቡ ቢሮው ከሚሰራቸው ተግባራት አንዱ በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ የሰላም ዕሴቶችን መገንባትና ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት ማድረግ መሆኑን ገልጸው፣39ኛው የአፍሪካ ሕብረት መሪዎች ስብሰባ በሰላም እንዲጠናቀቅ በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ አደረጃጀቶች በየአካባቢያቸው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የከተማዋን ሰላምና ደህንነት ለመጠበቅ አስተዋፅኦ አድርገዋል።
ኃላፊው እንዳሉት የዛሬው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና የሲቪክና የሙያ ማህበራት በዋናነት በኢኮኖሚያዊና ልማታዊ እንቅስቃሴዎች፣ በሰላም ጉዳዮች እና በዲሞክራሲያዊ ግንባታ ስርዓት ውስጥ የአባላቶቻቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ያለመ መሆኑን እና ማህበራቱ በሰላምና ፀጥታ ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማጠናከር፣ የህግ ማዕቀፎችን እና የአስተዳደር ሂደቶችን ለማብራራት እንዲሁም በህዝብ ተሳትፎ ላይ የተመሰረተ የፀጥታ አጠባበቅ ሥርዓትን ለማጠናከር እንደሆነም ተናግረዋል።
ስልጠናውን የሰጡት አቶ ገ/ስላሴ ገ/ሚካሄል የየሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን፣የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ድጋፍና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚ ሲሆኑ፣ በገለጻቸውም ወቅት፣የማህበረሰብ ድርጅቶች በአዋጅ ቁጥር 1113/2011 ላይ ሰፊ ገለጻ በመስጠት፣ ድርጅቶቹ በሀገሪቱ ልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያላቸውን ሚና እንዲያጎረብቱ እንዲሁም ተግባራቸው ከህጉ ጋር ተመጣጣኝ እንዲሆን አመልክተዋል።
የስልጠናው ዋና ዓላማ የድርጅቶችን ተጠያቂነት ማጠናከርና የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ሲሆን፣ በተጨማሪም የበጎ አድራጎትና የበጎ ፈቃደኝነት ባህል እንዲዳብር ለማስፈን እንደሆነም አሰልጣኙ አብራርተዋል።
በስልጠናው ላይም የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ም/ል ቢሮ ኃላፊና የህዝብ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍሰሐ ጥበቡ፣የሲቪክ ማህበራት ባለስልጣን ድርጅቶች ድጋፍና አገልግሎት መሪ ስራ አስፈጻሚና አባላቶች፣ከማዕከል እስከ ወረዳ ያሉት የዘርፉ ዳይሬክተር፣አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።