የተሳለጠ_አገልግሎት_ለላቀ_እርካታ
በአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ በስኬት እየተከናወነ ይገኛል
**
ጥር 27/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የህዝብ አገልግሎት ቀናትን መሰረት በማድረግ፣ በዛሬው ዕለት ተገልጋዮችን በአንድ ማዕከል በልዩ ትኩረት እያስተናገደ ይገኛል።
የቢሮው ከፍተኛ አመራሮች በአገልግሎት መስጫ ማዕከሉ በአካል በመገኘት የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱን በቅርበት ተከታትለዋል፤ አመራሮቹ በቦታው ተገኝተው ተገልጋዮችን በማነጋገርና ጉዳያቸውን ምላሽ እንዲያገኝ በማድረግ፣ ቢሮው ለህዝብ አገልግሎት የሰጠውን ትልቅ ዋጋ በተግባር በማሳየት ላይ ይገኛሉ።