በከተማው ውስጥ የሚገኙ የ14ኛ ዙር ብሄራዊ በጎ...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

በከተማው ውስጥ የሚገኙ የ14ኛ ዙር ብሄራዊ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ከ1ኛ እስከ 13ኛ ዙር ካሉ ነባር ወጣቶች የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

በከተማው ውስጥ የሚገኙ የ14ኛ ዙር ብሄራዊ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ከ1ኛ እስከ 13ኛ ዙር ካሉ ነባር ወጣቶች የልምድ ልውውጥ አደረጉ።

           ጥር 20/2018 (አ.አ.ሰፀ.አስ.ቢሮ)
                              *
የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ለብሄራዊ በጎፍቃደኛ ወጣቶች የልምድ ልውውጥና የተሞክሮ መድረክ አካሂዷል ።

መድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ግንባታ ዘርፍ ም/ቢሮ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ረታ ብሔራዊ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ፍቅር፣ አብሮነትና ወንድማማችነትን የሚያሳይ መሆኑን አንስተው በፍቃደኝነት ይህ የበጎ ፍቃደኝነት ስራ ለመስራት የመጡትን ወጣቶች እና ለዚህ ስራ አስተባባሪ የሆኑትን አካላት አመስግነዋል።

የክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድን የለውጥ ካርታ ይዘን በጎ ፈቃደኝነትን ይፋ ካደረጉበት ተግባራዊ ያደረጉት አንዱ፤ ዘላቂ ሰላምን፣ ዕርቅን፣ በመደመር እና ማህበራዊ ትስስርን በማስፈን ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን  ማድረግ ነውና
 የብሄራዊ የበጎ ፈቃድ ወጣቶች አገልግሎት ፕሮግራም ዋና አላማም ሀገራዊ አንድነትን እና ውህድትን ማሳደግ፣ሰላማዊ አብሮነትና ማህበራዊ ትስስር  መፍጠር እንዲሁም በክህሎት እና በብቃት ማጎልበት መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ብርሃኑ አክለውም በተለያዩ ሙያ ሰልጥናቸው ብትመጡም እውቀት በትምህርት ብቻ ሳይሆን በልምድና በምርጥ ተሞክሮ መገኘቱን እና የተለያዩ ቋንቋና ባህል መልመድ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ  መሆኑን ጠቁመው፤ ከተማችን ብሎም ሀገራችን ፍቅርና አብሮነት የፀናበት ለማድረግ የብሄራዊና ሀገራዊ አንድነት ሚዛኑን በመጠበቅ የዘመናትን ቋጠሮ በመፍታት የኢትዮጵያዊነት እና የመደመር ትውልድ እውን ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ስለ ምርጥ ተሞክሮ ቅመራ ሰነድ በአቶ መሉቀን እንየው 
የሰላም እሴት ግንባታና ብዝሀነት አያያዝ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ ላይም የሁሉም ክፍለከተማ የዘርፉ አስተባባሪዎች የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ጽ/ቤት የዘርፉ ቡድን መሪዎችና የስራ አስተባባሪዎች፣ ነባሮችና የ14ኛ ዙር ብሄራዊ በጎ ፍቃደኛ ወጣቶች ተገኝተዋል።