የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበር እና የመልካም አስተዳደር ክላስተር የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበር እና የመልካም አስተዳደር ክላስተር የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ።
ጥር 15/2018 ዓ.ም (ሰ.ፀ.አስ.ቢሮ)
**
በከተማው አስተዳደር በክላስተር ተወስኖ ወደ ትግበራ የገባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህግ ማስከበር እና የመልካም አስተዳደር ክላስተር የ6 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም በዛሬው እለት ገምግሟል።
በግምገማው ላይ የተገኙት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊና የክላስተሩ ሰብሳቢ እንዳሉት በከተማው አስተዳደር በተያዘው በጀት አመት ተቋማት ከተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት ጎን ለጎን በቅንጅት ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ ተምሳሌት ቀጣይነት ያለውና ግቡን የመታ ስራዎችን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር የቅንጅት ስርአቱን በማዘመን ከተማ አቀፍ በሆኑ አጀንዳዎች ላይ ወጥነት ያለው ስራን ለመስራት ያግዛል በማለት ወደ ትግበራ መግባቱን ኃላፊዋ በማስታወስ
የህግ ማስከበር ክላስተሩ የትግበራ አፈጻጸሙን የጋራ በማድረግ በአጋርነት የትራንስፖርት ፍሰቱን በማዘመን የህብረተሰቡን ምሬት ለመቀነስ ተርሚናሎችን ስርአት የማስያዝ ብሎም የስርቆት ዝርፊያና ንጥቂያዎች የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴዎች የመቆጣጠር፣የግብር አሰባሰቡና የግብይት ስርዓቱ እንዲዘምን በማድረግ፣የአደባባይ በዓላት በሰላም ተከብረው እንዲውሉ የማስቻል ህገ ወጥ ነጋዴዎችን የመቆጣጠር፣ህብረተሰቡን የሰላም ባለቤት የማድረግ የጸረ ሰላም ሀይሎችን ሴራ የመቆጣጠር፣ህገ ወጥ የመሬት ወረራዎች፣ አዋኪ ድርጊቶች የብሔራዊና የደህንነት ብሎም የከተማውን ገጽታ የቀየረውን የኮሪደር ልማት ስራዎች ብልሽት እንዳይገጥማቸው የማድረግ ከሸገር ከተማ አስተዳደሮች ጋር በቅንጅት በመሰራቱ፣የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር ላይም እርምጃ የመውሰድ ስራ በክላስተሩ ባለፉት 6ወራት የተሰሩት ዋና ዋና ስራዎች መሆናቸውን ኃላፊዋ ገልፀዋል።
ባጠቃላይ ክላስተሩ ከተቋቋመ ጀምሮ በተጠናከረ መልኩ በመቀናጀት በህግና ስርዓት የሚመራ ከተማ መፍጠር እንደተቻለ ህብረተሰቡ በሰላም ወቶ የሚገባበት የነዋሪውን ንቃተ ህሊና ከፍ በማድረግ ሌብነትና ጉበኝነትን የሚጸየፍ ከማድረግ አንጻር ውጤታማ መሆን የተቻለባቸው ወራቶች እንደነበሩም ጠቁመዉ በቀጣይም የጋራ ስራዎቻችን ላይ እርብርብ በማድረግ የከተማውን ህግና ስርዓት አጠናክሮ በማስከበር የህብረተሰቡን ደህንነት ማስጠበቅ እንደሚገባ ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የክላስተሩ ሰብሳቢና የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ አብራርተዋል ።
በህግ ማስከበሩ ክላስተር የተሰሩ ስራዎችን አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት ወ/ሮ አለም ጸሀይ ማሞ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የአገልግሎት ስታንዳርዳይዜሽን ዝግጅት ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲሆኑ በቀረበው ዕቅድ ሪፖርት ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎ በክብርት ኃላፊዋ ቀጣይ በክላስተሩ በሚሰሩ ስራዎች ላይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።