ከሸገር ከተማ ፀጥታና አስተዳደር ጋር በቅንጅት...

image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
image description
- recent news   

ከሸገር ከተማ ፀጥታና አስተዳደር ጋር በቅንጅት በመሰራቱ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበትና በህግና በስርአት የሚመሩ ከተሞችን መፍጠር መቻሉ ተገለፀ ።

ከሸገር ከተማ ፀጥታና አስተዳደር ጋር በቅንጅት በመሰራቱ የህግ የበላይነት የተረጋገጠበትና በህግና በስርአት የሚመሩ ከተሞችን መፍጠር መቻሉ ተገለፀ ።
  
ጥር 6/2018 ዓ.ም (አዲስ አበባ)
    ***
የከተማውን ሰላም በዘላቂነት ለማስቀጠል ብሎም ከተማዋን የሚመጥን የጸጥታ አጠባበቅ እንዲኖር ለማስቻል የአዲስ  አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ቢሮው በዛሬው ዕለትም ከሸገር ከተማ ጋር በ6 ወራት በቅንጅት በተሰሩ የፀጥታና የህግ የበላይነት በማስከበር ሂደት የተሰሩ ስራዎችን እንዲሁም የጥምቀት በዓል እቅድ ውይይት ላይ የጋራ የምክክር መድረክ ተደረገ። 

በውይይቱ ላይ በመገኝት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዳሉት የሁለቱንም ከተሞች አሰራር በማጠናከር በከተማው ላይ እንደ ሀገር የተከናወኑ አለማቀፍና ሀገር አቀፍ ጉባኤዎች ሁነቶች ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲያልፉ ከማድረጉ ጎን ለጎን ህብረተሰቡን በዋነኝነት የሰላም ባለቤት በማድረግ ቅንጅታዊ ስራዎችን በማጠናከር በጋራ በመሰራቱ ወንጀሎችንና የጸረ ሰላም ሽብር ሀይሎችን ሴራ ማክሸፍ መቻሉን ኃላፊዋ ጠቅሰው

የጸጥታው ስራ ወጥነት ባለው መልኩ እንዲሰራና ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ስምሪት በመስጠት እንደ ቢሮም ደግሞ የሰላም ሰራዊቱን አደረጃጀት በጋራ በማጠናከር ወንጀሎችን ቀድሞ በመከላከል አካባቢን በመጠበቅ ባለፉት ወራት ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረ ብሔራዊ አንድነታችንን ለአለም ህዝብ ያሳየንበት ነበርም ሲሉ የተደመጡ ሲሆን የንግድ ስራው ቁጥጥሩን በማጠናከር ህገ ወጥ የንግድ ግብይት እንዳይፈጠር የኑሮ ውድነት እንዳይባባስ ለማድረግ አምራቹና ሸማቹ ማህበረሰብ በቀጥታ እንዲገናኙ የማድረግና የግብይት ስርዓቱ በተቀላጠፈ መልኩ እንዲከናወን በተገቢው መንገድ ከሸገር አስተዳደር ጋር መሰራቱን አንስተዋል 

ኃላፊዋ አያይዘውም የህግ የበላይነትን በሁለቱም ከተሞችና ተቋማት ላይ በማስፈንና በርብርብ በመሰራታቸው በህግ የሚመራ ህብረተሰቡ ማፍራት እንደተቻለ ሁሉ የጸጥታው ስራ ቀጣይነት ያለው እንዲሆን ጸጥታን የሚያደፈርሱ አዝማሚያዎች ቀድሞ በመለየት ከፊታችን የሚከበሩና በከተማና በሀገር ደረጃ የሚሰሩና የሚከናወኑ በዓላት እንዲሁም 7ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆነው እንዲከናወኑ ቀደም ተብሎ ከተሰራው ስራ በበለጠ መልኩ እንድነትንና ቁርጠንነትን በሚያጎለብት መልኩ ቁርጠኝነትን የሚጠይቅ እንደ መሆኑ መጠን በቀጣይም ቅንጅታዊ ስራዎቻችንን በማጠናከር ለሀገር ሰላም በትብብር በመሆን በጋራ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ሀሳባቸውን ገልጸዋል ።

በመድረኩ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት ዶክተር ተሾመ አዱኛ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በም/ፕሬዝዳንት ማዕረግ የሸገር ከተማ ከንቲባ በበኩላቸው ሸገር ከተማ ከተቋቋመ ጀምሮ እንደ ሀገር በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን በማስታወስ የሁሉም መነሻና የጥንካሬ መሰረት ከተማ እንደ መሆኑ በዕውቀትና በቴክኖሎጂ በመደገፍ ከተሞች ከተማ እንዲሆኑ በጸጥታው ስራ ላይ ተጠናክሮ በመስራት ዘላቂነትን በማጠናከር የመጣውን ለውጥ አጠናክሮ በማስቀጠል አብሮነታችን ቀጣይነት እንዲኖረው በማድረግ የተጀመረውን የትምህርት፣የልማት የሀብት አጠቃቀሞችን አጠናክሮ በማስቀጠል ሰላምን በጋራ ጠብቅ ማስኬድ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።

በመጨረሻም ሁለቱም ኃላፊዎች መድረኩን በመሩበት ወቅት እንደተናገሩት የተቋማቱን ተግባሮች በማስተዋወቅና በጋራ በመሰራቱ እየታየ ያለውን የጸጥታ አጠባበቅ ስራ የተሻለ ውጤት ያመጣ ስራ በመኖሩ ከጸጥታው ጎን ለጎንም በመልካም አስተዳደር የሚነሱ ቅሬታዎችን በመፍታት ለሀገር ገጽታ በመገንባት የዜጎችን ሰላም ማረጋገጥ ይገባል በማለት ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

በ2018ዓ.ም በሁለቱም ተቋማት በቅንጅት በስድስት ወራት ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ ዕቅድ ሪፖርቱን ያቀረቡት አቶ ደሳለኝ ስዩም የሸገር ከተማ ጸጥታና አስተዳደር ጽ/ቤት ም/ሀላፊ ሲሆኑ እንዲሁም የከተራና የጥምቀት በዓል አከባበርን ማስፈጸሚያ ዕቅድ በተመለከተ ገለፃ ያደረጉት አቶ ተስፋዬ ደንድር የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ የጸጥታና ኦፕሬሽን ዘርፍ ኃላፊ ሲሆኑ በቀረበው ሪፖርትና ማስፈጸሚያ ዕቅዱ ላይ ሰፊ ውይይትም ተደርጎበታል።

በውይይቱ ላይ ዶክተር ተሾመ አዱኛ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በም/ፕሬዝዳንት ማእረግ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ና የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል፣ክብርት ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ የአዲስ አበባ ከተማ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ፣አቶ ደሳለኝ ስዩም የሸገር ከተማ ጸጥታና አስተዳደር ጽ/ቤት ም/ኃላፊ፣ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ኃላፊ፣ም/ኮምሽነር ፍቅሩ አለማየሁ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ም/አዛዥ፣ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ የአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ኮምሽነር አህመድ መሃመድ የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ኮምሽነር፤የሁለቱም ከተሞች የአጎራባች ክ/ከተሞች ስራ አስፈፃሚና አስተዳዳሪዎች የሁለቱም ከተሞች ፖሊስ መምሪያ አዛዦች፤ የደንብ ማስከበር አመራሮች፤ የሰላምና ጸጥታ የክፍለ ከተማ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና አመራሮች ተገኝተዋል ።